Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ቆሮንቶስ 11:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ሳይገባው የሚበላና የሚጠጣ የጌታን ሥጋ ስለማይለይ ለራሱ ፍርድ ይበላል፤ ይጠጣልም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ምክንያቱም ማንም የጌታን ሥጋ ሳይገባው ቢበላና ቢጠጣ ፍርድ የሚያመጣበትን ይበላል፤ ይጠጣልም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ማንም ሰው የጌታ ሥጋ ምን መሆኑን ለይቶ ሳያውቅ የጌታን ኅብስት ቢበላና የጌታን ጽዋ ቢጠጣ በራሱ ላይ ፍርድን ያመጣል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ሳይ​ገ​ባው፥ የጌ​ታ​ችን ሥጋም እንደ ሆነ ሳያ​ውቅ፥ ሰው​ነ​ቱ​ንም ሳያ​ነጻ፥ የሚ​በ​ላና የሚ​ጠጣ ለራሱ ፍር​ዱ​ንና መቅ​ሠ​ፍ​ቱን ይበ​ላል፤ ይጠ​ጣ​ልም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ሳይገባው የሚበላና የሚጠጣ የጌታን ሥጋ ስለማይለይ ለራሱ ፍርድ ይበላልና፥ ይጠጣልምና።

Ver Capítulo Copiar




1 ቆሮንቶስ 11:29
11 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ ያልተገባ ሆኖ ሳለ ይህን ኅብስት የበላ ወይም የጌታን ጽዋ የጠጣ ሁሉ የጌታ ሥጋና ደም ዕዳ አለበት።


በዚሁ ምክንያት ከእናንተ መካከል ብዙዎች የደከሙና የታመሙ አሉ፥ አያሌዎችም አንቀላፍተዋል።


ወንድሞቼ ሆይ! ከእናንተ ብዙዎች አስተማሪዎች አይሁኑ፤ ምክንያቱም አስተማሪዎች የሆንን የባሰ ፍርድ እንደምንቀበል ታውቃላችሁ።


ጠንካራ ምግብ የሚያስፈልጋቸው ግን መልካሙንና ክፉውን የመለየት ልምድ ያላቸው ብስለት ያላቸው ሰዎች ናቸው።


አመሰገነ ቆርሶም “እንካችሁ ብሉ፤ ይህ ስለ እናንተ የሚሆን ሥጋዬ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት፤” አለ።


ስለዚህ ባለ ሥልጣንን የሚቃወም የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ይቃወማል፤ የሚቃወሙትም በራሳቸው ላይ ፍርድን ይቀበላሉ።


ትእዛዝን የሚጠብቅ ክፉ ነገር አይገጥመውም፥ የጠቢብም ልብ ጊዜንና ፍርድን ያውቃል።


ከሁሉም በላይ ወንድሞቼ ሆይ! በሰማይ ወይም በምድር ወይም በማናቸውም ነገር ቢሆን አትማሉ፤ ነገር ግን ከፍርድ በታች እንዳትወድቁ፥ ነገራችሁ “አዎ” ቢሆን አዎ ይሁን፤ “አይደለም” ቢሆን አይደለም ይሁን።


የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ መጣ፥ እናንተም “እነሆ፥ በላተኛና የወይን ጠጅ ጠጭ፤ የቀራጮችና የኀጢአተኞች ወዳጅ ነው፤” አላችሁ።


ሰው ግን ራሱን ይመርምር፤ እንዲሁም ከኅብስቱ ይብላ፤ ከጽዋውም ይጠጣ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios