La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 16:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከእስራኤልም ልጆች ሁለት መቶ ኀምሳ ሰዎች የሆኑ ከጉባኤው የተመረጡ፥ በዝናቸውም የገነኑ የማኅበሩ አለቆች ጋር በመሆን እነርሱ በሙሴ ላይ ተነሡ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሙሴን ተቃወሙት። ከእነዚህም ጋራ ታዋቂ የማኅበረ ሰቡ መሪዎች የሆኑና በጉባኤ አባልነት የተመረጡ ሁለት መቶ ዐምሳ እስራኤላውያን ዐብረው ነበሩ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከእነርሱም ጋር በእስራኤላውያን ዘንድ ዝናቸው የታወቀና ለሕዝብ መሪነት የተመረጡ ሁለት መቶ ኀምሳ ሰዎችን ወስደው በሙሴ ላይ ተነሡ፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በሙ​ሴም ላይ ተነሡ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በም​ክር የተ​መ​ረጡ፥ ዝና​ቸ​ውም የተ​ሰማ ሁለት መቶ አምሳ የማ​ኅ​በሩ አለ​ቆች ከእ​ነ​ርሱ ጋር ነበሩ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከእስራኤልም ልጆች ሁለት መቶ አምሳ ሰዎች ከእነርሱ ጋር ወሰዱ፤ ከጉባኤው የተመረጡ ዝናቸውም የተሰማ የማኅበሩ አለቆች ነበሩ።

Ver Capítulo



ዘኍል 16:2
10 Referencias Cruzadas  

በዚያን ዘመን ኔፊሊም በምድር ላይ ነበሩ፥ እና ከዚያም በኋላ የእግዚአብሔር ልጆች የሰውን ሴቶች ልጆች ባገቡ ጊዜ ልጆችን ወለዱላቸው፥ እነርሱም በዱሮ ዘመን፥ ስማቸው የታወቀ፥ ኃያላን ሆኑ።


ጽኑዓን ኃያልን የሆኑ በአባቶቻቸውም ቤት የታወቁ የኤፍሬም ልጆች ሀያ ሺህ ስምንት መቶ ነበሩ።


የአባቶቻቸውም ቤቶች አለቆች እነዚህ ነበሩ፤ ዔፌር፥ ይሽዒ፥ ኤሊኤል፥ ዓዝርኤል፥ ኤርምያ፥ ሆዳይዋ፥ ኢየድኤል፤ እነርሱ ጽኑዓን ኃያላን የታወቁ ሰዎች የአባቶቻቸውም ቤቶች አለቆች ነበሩ።


በአንቺ ላይ ካኖርኋት ከውበቴ የተነሣ ውበትሽ ፍጹም ነበረና ስምሽ በሕዝቦች መካከል ወጣ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


እነርሱም ዕራቁትነትዋን ገለጡ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችዋንም ወሰዱ፤ እርሷንም በሰይፍ ገደሉ፤ በሴቶች መካከል መተረቻ ሆነች፥ ፍርድም ተፈጸመባት።


ከማኅበሩ የተመረጡ የእስራኤል የወገኖቻቸው አውራዎች፥ የአባቶቻቸው ነገድ አለቆች እነዚህ ነበሩ።


ሙሴም ኢትዮጵያይቱን በእርግጥ አግብቶአልና ባገባት በኢትዮጵያይቱ ምክንያት ማርያምና አሮን በእርሱ ላይ ተናገሩ።


እሳትም ከጌታ ዘንድ ወጥቶ ያጥኑ የነበሩትን ሁለት መቶ ኀምሳ ሰዎች በላቸው።


የኤልያብም ልጆች፤ ነሙኤል፥ ዳታን፥ አቤሮን ናቸው፤ እነዚህ ዳታንና አቤሮን ከማኅበሩ የተመረጡ ነበሩ፤ ቆሬን ከተከተሉት ሰዎች ጋር በመሆን በጌታ ላይ ባመፁ ጊዜ ሙሴንና አሮንን የተገዳደሩ ነበሩ፤


“አባታችን በምድረ በዳ ሞተ፤ በራሱ ኃጢአት ሞተ እንጂ ቆሬን በመከተል በጌታ ላይ ከተሰበሰቡት ሰዎች መካከል አልነበረም፤ ወንዶችም ልጆች አልነበሩትም።