ሕዝቅኤል 23:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 እነርሱም ዕራቁትነትዋን ገለጡ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችዋንም ወሰዱ፤ እርሷንም በሰይፍ ገደሉ፤ በሴቶች መካከል መተረቻ ሆነች፥ ፍርድም ተፈጸመባት። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 እነርሱም ዕርቃን አስቀሯት፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቿን ነጠቋት፤ እርሷንም በሰይፍ ገደሏት፤ በሴቶችም ዘንድ መተረቻ ሆና ቀረች፤ ፍርድም ተፈጸመባት። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 እነርሱም ልብስዋን ገፈው እርቃንዋን አስቀሩአት፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችዋን በምርኮ ያዙ፤ እርስዋንም በሰይፍ ገደሉአት፤ ፍርድም በእርስዋ ላይ ተግባራዊ ሆነ፤ ሴቶች ሁሉ ስለ ገጠማት መጥፎ ዕድል አሉባልታ ማሰማት ጀመሩ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 እነርሱም ኀፍረተ ሥጋዋን ገለጡ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችዋንም ማርከው ወሰዱ፤ እርስዋንም በሰይፍ ገደሉ፤ በእርስዋና በሴቶች ልጆችዋ ላይ በቀልን ስላደረጉባቸው በሴቶች መካከል መተረቻ ሆነች። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 እነርሱም ኅፍረተ ሥጋዋን ገለጡ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችዋንም ማርከው ወሰዱ፥ እርስዋንም በሰይፍ ገደሉ፥ ፍርድንም ስላደረጉባት በሴቶች መካከል መተረቻ ሆነች። Ver Capítulo |