ዘኍል 13:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም የከነዓንን ምድር እንዲሰልሉ ላካቸው፥ እነርሱንም እንዲህ አላቸው፦ “ከዚህ በኔጌብ በኩል አድርጋችሁ ውጡ፥ ወደ ተራራማውም አገር ሂዱ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴም ከነዓንን እንዲሰልሉ በላካቸው ጊዜ እንዲህ አላቸው፤ “ኔጌብን ዘልቃችሁ ወደ ተራራማው አገር ግቡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴም ሲልካቸው እንዲህ አላቸው፦ “በኔጌብ በኩል አድርጋችሁ ወደ ተራራማው አገር ውጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም የከነዓንን ምድር ይሰልሉ ዘንድ ላካቸው፤ አላቸውም፥ “ከዚህ ወደ ምድረ በዳ ሂዱ፥ ወደ ተራሮችም ውጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም የከነዓንን ምድር ይሰልሉ ዘንድ ላካቸው፥ አላቸውም፦ ከዚህ በደቡብ በኩል ውጡ፥ ወደ ተራሮችም ሂዱ፤ |
በደቡብም ምድር አማሌቅ ተቀምጦአል፤ በተራሮቹም ኬጢያዊና ኢያቡሳዊ አሞራዊም ተቀምጠዋል፤ ከነዓናዊም በባሕር ዳርና በዮርዳኖስ አጠገብ ተቀምጦአል።”
በማግስቱም ማልደው ተነሡ፥ ወደ ተራራውም ራስ እንዲህ እያሉ ወጡ፦ እነሆ፥ እኛ በዚህ አለን፤ እኛ ኃጢአትን ሠርተናልና ጌታ ወዳለው ስፍራ እንወጣለን።
በዚያም በተራራማው አገር ይኖሩ የነበር አሞራውያን ወጥተው ተጋጠሙአችሁ፥ እንደ ንብ መንጋ አሳደዱአችሁ፥ እስከ ሔርማም ድረስ በሴይር ድል ነሷችሁ።
እንዲሁም ኢያሱ ምድሪቱን ሁሉ ተራራማውን አገር ደቡቡንም ቈላውንም የተዳፋቱንም ስፍራ ነገሥታቶቻቸውንም ሁሉ መታ፤ ማንንም አላስቀረም፤ የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዳዘዘውም እስትንፋስ ያለውንም ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ።
ከዚያም በአቅረቢም ዐቀበት በደቡብ በኩል ወጣ፥ ወደ ጺንም አለፈ፥ በቃዴስ በርኔ ወደ ደቡብ በኩል ወጣ፥ በሐጽሮንም በኩል አለፈ፥ ወደ አዳርም ወጣ፥ ወደ ቀርቃ ዞረ፥
የነዌም ልጅ ኢያሱ ከሰጢም ሁለት ሰላዮች በስውር እንዲህ ብሎ ላከ፦ “ሄዱ፥ ምድሪቱንና ኢያሪኮን እዩ።” ሄዱም፤ ረዓብም ወደሚሉአት አመንዝራ ቤት ገቡ፥ በዚያም አደሩ።
እርሷም “የሰጠኸኝ የኔጌብ መሬት በመሆኑ፥ የውሃ ምንጮችን እንድትሰጠኝ እለምንሃለሁ” አለችው፤ ካሌብም የላይኛውንና የታችኛውን ምንጮች ሰጣት።
ጌታ ከይሁዳ ሰዎች ጋር ነበር፤ ስለዚህ ኰረብታማውን አገር ያዙ፤ ነገር ግን በረባዳማው ምድር የሚኖሩት ሰዎች ከብረት የተሠሩ ሠረገሎች ስለ ነበሯቸው ከዚያ አሳደው ሊያስወጧቸው አልቻሉም።