ነህምያ 6:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በተጨማሪም መልካም ሥራውን በፊቴ ይናገሩ ነበር፥ እኔ ያልሁትንም ለእርሱ ይነግሩት ነበር፤ ጦቢያም ሊያስፈራራኝ ደብዳቤዎችን ይልክ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህም በተጨማሪ ስለ መልካም ሥራው በየጊዜው ይነግሩኝና እኔም ያልሁትን ይነግሩት ነበር፤ ጦቢያም እኔን ለማስፈራራት ደብዳቤ ይልክብኝ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጦቢያ ያደረገውን መልካም ነገር በማጋነን በፊቴ እንኳ ሳይቀር ይናገሩለት ነበር፤ እኔም የምለውን ሁሉ ለእርሱ ይነግሩት ነበር፤ ከዚህም የተነሣ እርሱ እኔን ለማስፈራራት ደብዳቤዎችን ከመላክ አልተቈጠበም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም በፊቴ ስለ እርሱ መልካምነት ይናገሩ ነበር፤ የእርሱን ነገር ወደ እኔ ያመጡ ነበር፤ የእኔንም ቃል ወደ እርሱ ይወስዱ ነበር፤ ጦቢያም ሊያስፈራራኝ ደብዳቤዎችን ይልክ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም በፊቴ ስለ እርሱ መልካም ይናገሩ ነበር፥ ቃሌንም ያወሩለት ነበር፥ ጦብያም ሊያስፈራራኝ ደብዳቤዎችን ይልክ ነበር። |
በይሁዳ ለእርሱ የማሉለት ብዙ ሰዎች ነበሩና፤ የአራሕ ልጅ የሼካንያ አማች ነበረና፥ ልጁ ይሆሐናንም የቤራክያን ልጅ የሜሹላምን ሴት ልጅ አግብቷልና።