ነህምያ 5:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በልቤም አሰብሁና መኳንንቶቹንና ሹማምቱን ተከራከርኋቸው፥ እንዲህም አልኋቸው፦ “እያንዳንዳችሁ ለወንድማችሁ በአራጣ ታበድራላችሁ”፤ ትልቅ ጉባኤም ሰበሰብሁባቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ነገሩን በሐሳቤ ካወጣሁ ካወረድሁ በኋላ፣ መኳንንቱንና ሹማምቱን ገሠጽኋቸው፤ “ከገዛ አገራችሁ ሰዎች ላይ እንዴት ዐራጣ ትበላላችሁ” አልኋቸውም። ስለዚህ ከእነርሱ ጋራ ለመነጋገር ታላቅ ስብሰባ ጠራሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ላደርገው የሚገባኝንም በልቤ ወስኜ የሕዝቡ መሪዎች የሆኑትን ባለሥልጣኖች “እናንተ እኮ የገዛ ወንድሞቻችሁን በመጨቈን አራጣ ታስከፍላላችሁ!” በማለት በቊጣ ገሠጽኳቸው። ለችግሩም መፍትሔ ለማግኘት ሕዝቡን በአንድነት ሰብስቤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በልቤም አሰብሁ፤ ታላላቆቹንና ሹሞቹንም፥ “ሁላችሁ እያንዳንዳችሁ ወለድ ትወስዳላችሁ” ብዬ ተጣላኋቸው፤ ትልቅም ጉባኤ ሰበሰብሁባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በልቤም አሰብሁ፥ ታላላቆቹንና ሹማምቱንም፦ ሁላችሁ እያንዳንዳችሁ ወለድ ትወስዳላችሁ ብዬ ተጣላኋቸው፥ ትልቅም ጉባኤ ሰበሰብሁባቸው። |
ደም ለማፍሰስ በአንቺ ውስጥ ጉቦን ተቀበሉ፥ አንቺም አራጣና ትርፍ ወስደሻል፥ ጎረቤቶችሽንም ጨቁነሽ የማይገባ ትርፍ አገኘሽ፥ እኔንም ረሳሽኝ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእስራኤል መሪዎች ሆይ፥ ይብቃችሁ፤ ግፍንና ጭቆናን አስወግዱ፥ ፍርድንና ጽድቅን አድርጉ፤ ቅሚያችሁን ከሕዝቤ ላይ አንሱ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ስለዚህ ከአሁን ጀምሮ ማንንም በሰብአዊ አመለካከት እንደምናየው አድርገን አንመለክትም፤ ክርስቶስንም በዚህ መልክ ተመልክተነው የነበርን ብንሆን እንኳን፥ ከእንግዲህ ወዲህ ግን በዚህ መልክ አይደለም የምናውቀው።