እነርሱም እርሷን አፈፍ አድርገው በመያዝ ወደ ቤተ መንግሥት ወሰዱአት፤ እዚያም የፈረስ መግቢያ ቅጽር በር ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ገደሉአት።
ነህምያ 3:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከ “የፈረሶች በር” በላይ ጀምሮ በየቤታቸው ትይዩ ያለውን ካህናቱ እያንዳንዳቸው አደሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የፈረስ በር ተብሎ ከሚጠራው በላይ ያለውን ደግሞ ካህናቱ እያንዳንዳቸው በየመኖሪያ ቤታቸው ትይዩ ያለውን መልሰው ሠሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌሎች ካህናትም እያንዳንዳቸው በየመኖሪያ ቤታቸው ፊት ለፊት ያለውን መስመር በመከተል ከፈረስ ቅጽር በር በስተሰሜን በኩል ያለውን ክፍል ሠሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከፈረሶች በር በላይ ካህናቱ እያንዳንዳቸው በየቤታቸው አንጻር ሠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከፈረሱ በር በላይ ካህናቱ እያንዳንዳቸው በየቤታቸው አንጻር አደሱ። |
እነርሱም እርሷን አፈፍ አድርገው በመያዝ ወደ ቤተ መንግሥት ወሰዱአት፤ እዚያም የፈረስ መግቢያ ቅጽር በር ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ገደሉአት።
ከእነርሱም በኋላ ብንያምና ሐሹብ ከቤታቸው ፊት ለፊት ያለውን አደሱ። ከእነርሱም በኋላ የአናንያ ልጅ የማዓሤያ ልጅ አዛርያ በቤቱ አጠገብ ያለውን አደሰ።
ከዚያ በኋላ የኢሜር ልጅ ጻዶቅ ከቤቱ ፊት ለፊት ያለውን አደሰ። ከእርሱም በኋላ “የምሥራቅ በር” ጠባቂ የሆነው የሼካኔያ ልጅ ሼማዔያ አደሰ።
የሬሳና የአመድ ሸለቆ ሁሉ፥ እስከ ቄድሮን ወንዝ ድረስ ያለው የትልም እርሻ ሁሉ፥ በምሥራቅም በኩል እስካለው እስከ ፈረሰ በር ማዕዘን ድርስ ለጌታ የተቀደሰ ይሆናል፤ ከእንግዲህም ወዲህ ለዘለዓለም አይነቀልም አይፈርስምም።”