ነህምያ 3:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአጠገቡ የሚጽጳ ገዢ የኢያሱ ልጅ ዔዜር በግንቡ መደገፊያ ወደ ጦር መሣሪያ ግምጃ ቤት መወጣጫ ፊት ለፊት ያለውን ሁለተኛውን ክፍል አደሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከርሱም ቀጥሎ ወደ ጦር መሣሪያ ግምጃ ቤት በሚያወጣውና እስከ ማእዘኑ በሚደርሰው ትይዩ ያለውን ሌላ ክፍል የምጽጳ ገዥ የኢያሱ ልጅ ኤጽር መልሶ ሠራ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምጽጳ ወረዳ ገዥ የሆነው የኢያሱ ልጅ ዔዜር በጦር መሣሪያው ግምጃ ቤት ፊት ለፊት ያለውን እስከ ቅጽሩ መመለሻ ማእዘን ድረስ ያለውን ሁሉ ሠራ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአጠገቡም የመሴፋ ገዢ የኢያሱ ልጅ አዙር በማዕዘኑ አጠገብ በመወጣጫው ግንብ አንጻር ያለውን ሌላውን ክፍል ሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአጠገቡም የምጽጳ አለቃ የኢያሱ ልጅ ኤጽር በማዕዘኑ አጠገብ በጦር መሣሪያ ቤት አንጻር ሌላውን ክፍል አደሰ። |
የሚጽጳም አውራጃ ገዢ የኮልሖዜ ልጅ ሻሉን “የምንጭ በር” አደሰ፤ መልሶ ሠራው፥ ከደነውም፥ በሮቹን አቆመ፥ ቁልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አበጀ፤ በንጉሡ አትክልት ቦታ አጠገብ ያለውን የሼላሕን መዋኛ ቅጥር ከዳዊት ከተማ ወደ ታች እስከሚወርደው ደረጃ ድረስ ሠራ።