ነህምያ 3:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእርሱም በኋላ ሌዋውያንና የባኒ ልጅ ሬሑም አደሱ። በአጠገቡ የቅዒላ አውራጃ እኩሌታ ገዢ ሐሻብያ ስለ አውራጃው ብሎ አደሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከርሱ ቀጥሎ ሌዋውያኑ በባኒ ልጅ በሬሁ ሥር ሆነው የዕድሳት ሥራ ሠሩ። ከርሱ ቀጥሎ የቅዒላ አውራጃ እኩሌታ ገዥ ሐሸብያ አውራጃውን መልሶ ሠራ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቅጽሩ ሥራ ተካፋዮች የነበሩት ሌዋውያን ስም ዝርዝር ከዚህ የሚከተለው ነው፦ የባኒ ልጅ ረሑም ከዚያ ቀጥሎ ያለውን ክፍል ሠራ። የቀዒላ ወረዳ እኩሌታ ገዢ የሆነው ሐሻብያ ወረዳውን በመወከል ቀጥሎ ያለውን ክፍል ሠራ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእርሱም በኋላ ሌዋውያንና የባኒ ልጅ ሬሁም ሠሩ። በአጠገባቸውም የቅዒላ ግዛት እኩሌታና የአውራጃዎችዋ ገዢ አሰብያ ሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእርሱም በኋላ ሌዋውያንና የባኒ ልጅ ሬሁም አደሱ። በአጠገባቸውም የቅዒላ ግዛት እኩሌታ አለቃ ሐሸብያ ስለ ግዛቱ አደሰ። |
ከእርሱም በኋላ የቤትጹር አውራጃ እኩሌታ ገዢ የሆነው የዓዝቡቅ ልጅ ነህምያ በዳዊት መቃብር ፊት ለፊት እስካለው ስፍራ፥ እስከ ተሠራው መዋኛ ስፍራና እስከ ኃያላኑ ቤት ድረስ አደሰ።