La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ነህምያ 3:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የቤትሐካሪም አውራጃ ገዢ የሬካብ ልጅ ማልኪያ “የፍግ በር” አደሰ፤ መልሶ ሠራው፥ በሮቹን አቆመ፥ ቁልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አበጀ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የቈሻሻ መጣያ በር ተብሎ የሚጠራው የቤትሐካሪም አውራጃ ገዥ የሆነው የሬካብ ልጅ መልክያ መልሶ ሠራ፤ መልሶ ከሠራ በኋላም መዝጊያዎቹን፣ መቀርቀሪያዎቹንና መወርወሪያዎቹን በየቦታቸው አኖረ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የቤትሀካሬም ወረዳ ገዢ የሆነው የሬካብ ልጅ ማልኪያ የጒድፍ መጣያውን ቅጽር በር በማደስ ሠራ፤ በሮችን ገጠመ፤ ለበሮቹም ቊልፎችንና መወርወሪያዎችን አበጀ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የቤ​ት​ሐ​ካ​ሪ​ምም ግዛት ገዢ የሬ​ካብ ልጅ መል​ክያ ከወ​ን​ድ​ሞ​ቹና ከል​ጆቹ ጋር የጕ​ድፍ መጣ​ያ​ውን በር ሠራ፤ ከደ​ነው፤ ሳን​ቃ​ዎ​ቹ​ንም አቆመ፤ ቍል​ፎ​ቹ​ንና መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አደ​ረገ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የቤትሐካሪምም ግዛት አለቃ የሬካብ ልጅ መልክያ የጉድፍ መጣያውን በር አደሰ፥ ሠራው፥ ሳንቃዎቹንም አቆመ፥ ቁልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አደረገ።

Ver Capítulo



ነህምያ 3:14
9 Referencias Cruzadas  

በዚህ ጊዜ የሳኦል ልጅ ኢያቡስቴ የወራሪ ጭፍራ ቡድን መሪዎች የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበሩት፤ አንዱ በዓና ሌላው ደግሞ ሬካብ ይባሉ ነበር። እነርሱም የበኤሮት ተወላጅ የሆነው የሬሞን ልጆች የነበሩ ሲሆን፥ በኤሮትም ከብንያም ክፍል እንደ አንዱ ተቆጥራ ነበር።


ኢዩ ተነሥቶ እንደገና ጉዞ ቀጠለ፤ በመንገድ ሳለም የሬካብን ልጅ ኢዮናዳብን አገኘ፤ ኢዩም ሰላምታ ከሰጠው በኋላ “እኔና አንተ በሐሳብ አንድ ነን፤ ታዲያ ከእኔ ጋር ትተባበራለህን?” ሲል ጠየቀው። ኢዮናዳብም “አዎ እተባበርሃለሁ” ሲል መለሰ። ኢዩም “እንግዲያውስ ጨብጠኝ” ሲል መለሰለት፤ እጅ ለእጅ ተያይዘው ኢዩ ደግፎት በሠረገላው ላይ አስቀመጠውና፥


የሚካኤል ልጅ፥ የበዓሤያ ልጅ፥ የመልክያ ልጅ፥


የይሁዳንም አለቆች ወደ ቅጥሩ ላይ አወጣኋቸው፥ አመስጋኞቹንም በሁለት ታላላቅ ተርታ አቆምኋቸው፥ አንዱም ወደ ቀኝ በቅጥሩ ላይ ወደ ጉድፍ መጣያው በር ሄደ።


በሌሊትም በሸለቆው በር ወጣሁ፥ ወደ “የዘንዶ ምንጭ” እና ወደ “የፍግ በር” ሄድኩ፤ የፈረሰውን የኢየሩሳሌምን ቅጥርና በእሳት የተቃጠሉትን በሮችዋን ተመለከትኩ።


በአጠገባቸውም የኢየሩሳሌም ግዛት እኩሌታ ገዢ የሁር ልጅ ሬፋያ አደሰ።


እናንተ የብንያም ልጆች ሆይ! ክፉ ነገር ታላቅም ጥፋት ከሰሜን ይጐበኛልና ከኢየሩሳሌም ውስጥ ለደህንነታችሁ ሽሹ፥ በቴቁሔ መለከቱን ንፉ፥ በቤትሐካሪም ላይ ምልክት አንሡ።