ነህምያ 13:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ ከሰንበት በፊት በኢየሩሳሌም በሮች ድንግዝግዝታ በሆነ ጊዜ በሮችዋ እንዲዘጉ፥ ሰንበትም እስኪያልፍ ድረስ እንዳይከፈቱ አዘዝሁ። በሰንበትም ቀን ሸክም እንዳይገባ ከብላቴኖቼ በአያሌዎቹ በሮችዋን አስጠበቅሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሰንበት ዋዜማ በኢየሩሳሌም በሮች ላይ የምሽቱ ጥላ ማረፍ ሲጀምር በሮቹ እንዲዘጉና፣ ሰንበት እስኪያልፍ ድረስ እንዳይከፈቱ አዘዝሁ፤ በሰንበት ቀን ጭነት እንዳይገባም ከራሴ ሰዎች አንዳንዶቹን በየበሩ ላይ አቆምሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ በሰንበት ዋዜማ መሸትሸት ሲል የከተማይቱ ቅጽር በሮች እንዲዘጉና የሰንበት ቀን ከማለፉም በፊት እንዳይከፈቱ ትእዛዝ ሰጠሁ፤ በሰንበት ቀን ወደ ከተማይቱ ምንም ሸክም እንዳይገባ ይቈጣጠሩ ዘንድ ከአገልጋዮቼ አንዳንዶቹን በቅጽር በሮች አሰማራሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህ በኋላ ሰንበት ከመግባቱ በፊት በኢየሩሳሌም በሮች ድንግዝግዝታ በሆነ ጊዜ በሮችዋ እንዲዘጉ፥ ሰንበትም እስኪያልፍ ድረስ እንዳይከፈቱ አዘዝሁ። በሰንበትም ቀን ሸክም እንዳይገባ ከብላቴኖች በዐያሌዎቹ በሮችዋን አስጠበቅሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚህ በኋላ ከሰንበት በፊት በኢየሩሳሌም በሮች ድንግዝግዝታ በሆነ ጊዜ በሮችዋ እንዲዘጉ፥ ሰንበትም እስኪያልፍ ድረስ እንዳይከፈቱ አዘዝሁ። በሰንበትም ቀን ሸክም እንዳይገባ ከብላቴኖቼ በአያሌዎቹ በሮችዋን አስጠበቅሁ። |
እኔም እንዲህ አልኋቸው፦ የኢየሩሳሌም በሮች ፀሐይ ሞቅ እስኪል ድረስ አይከፈቱ፥ በሚቆሙበት ጊዜ በሮቹን ይዝጉ፥ ይቆልፉትም፤ ከኢየሩሳሌም ነዋሪዎች አንዳንዱን በተራው አንዳንዱን ደግሞ በየቤቱ አጠገብ ጠባቂዎች ይሾሙ።
“የምድራችሁንም መከር በምትሰበስቡበት ጊዜ እስከ እርሻችሁ ድንበር ድረስ ፈጽማችሁ አትሰብስቡ። የመከሩንም ቃርሚያ አትልቀሙ፤ ለድሀውና ለእንግዳው ተዉት። እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ።”