ነህምያ 12:47 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤልም ሁሉ በዘሩባቤልና በነህምያ ዘመን ለመዘምራኑና ለበረኞቹ እድል ፈንታቸውን በየዕለቱ ይሰጡ ነበር፥ የተቀደሰውንም ነገር ለሌዋውያን ሰጡ፥ ሌዋውያኑም ከተቀደሰው ነገር ለአሮን ልጆች ሰጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዘሩባቤልና በነህምያም ዘመን እስራኤል ሁሉ ለመዘምራኑና ለበር ጠባቂዎቹ የየዕለቱን ድርሻ ይሰጡ ነበር፤ የሌሎቹን ሌዋውያን ድርሻም ለብቻ ያስቀምጡ ነበር፤ ሌዋውያኑም ለአሮን ዘሮች ድርሻቸውን ያስቀምጡላቸው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዘሩባቤልና በነህምያ ዘመን መላው እስራኤላውያን ለቤተ መቅደሱ መዘምራንና ለዘብ ጠባቂዎቹ የየዕለት ድርሻቸውን ይሰጡ ነበር፤ ሌዋውያኑም የአሮን ተወላጁን ድርሻ ይሰጡ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስራኤልም ሁሉ በዘሩባቤልና በነህምያ ዘመን ለመዘምራኑና ለበረኞቹ ፈንታቸውን በየዕለቱ ይሰጡ ነበር፤ የተቀደሰውንም ነገር ለሌዋውያን ሰጡ፤ ሌዋውያኑም ከተቀደሰው ነገር ለአሮን ልጆች ሰጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስራኤልም ሁሉ በዘሩባቤልና በነህምያ ዘመን ለመዘምራኑና ለበረኞቹ እድል ፈንታቸውን በየዕለቱ ይሰጡ ነበር፥ የተቀደሰውንም ነገር ለሌዋውያን ሰጡ፥ ሌዋውያኑም ከተቀደሰው ነገር ለአሮን ልጆች ሰጡ። |
ከዚያም በኋላ ከሶርያውያን ሰፈር በመነሣት ወደ ሰማርያ ተመልሰው ሄዱ፤ እዚያም እንደ ደረሱ የከተማይቱን ቅጽር በር ዘበኞች ጠርተው “ወደ ሶርያውያን ሰፈር ሄደን ነበር፤ ነገር ግን ምንም ያየነው ሰው ወይም የሰማነው ድምፅ እንኳ የለም፤ ፈረሶችና አህዮች እንደ ታሰሩ ናቸው፤ ድንኳኖቹም ሶርያውያን ትተዋቸው ስለ ሄዱ ባዶአቸውን ናቸው” ሲሉ ነገሩአቸው።
ከዘሩባቤል፥ ከኢያሱ፥ ከነህምያ፥ ከሠራያ፥ ከረዔላያ፥ ከመርዶክዮስ፥ ከቢልሻን፥ ከሚስፋር፥ ከቢግዋይ፥ ከሬሁምና፥ ከባዓና ጋር መጡ። የእስራኤልም ሕዝብ ሰዎች ቍጥር ይህ ነው።