ነህምያ 11:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምስጋናውን በጸሎት ለመጀመር መሪ የነበረው የአሳፍ ልጅ፥ የዛብዲ ልጅ፥ የሚካ ልጅ ማታንያ፤ ከወንድሞቹ ሁለተኛ የነበረው ባቅቡቅያ፤ የይዱቱን ልጅ፥ የጋላል ልጅ፥ የሻሙዓ ልጅ ዓብዳ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በምስጋናና በጸሎት ጊዜ ይመራ የነበረው የዋናው አለቃ የአሳፍ ልጅ፣ የዘብዲ ልጅ፣ የሚካ ልጅ መታንያ፣ ከወንድሞቹ ሁለተኛ የሆነው በቅቡቅያ፣ የኤዶታም ልጅ፣ የጋላል ልጅ፣ የሳሙስ ልጅ አብድያ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማታንያ የሚካ ልጅ፥ የዘብዲ ልጅ፥ የመዘምራን አለቃ የነበረው የአሳፍ ልጅ፥ የእርሱ ምክትል የነበረው የባቅቡቅያ ልጅና፥ የሻሙዐ ልጅ የነበረው ዐብዳ፥ የጋላል ልጅ፥ የዩዱቱን ልጅ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጸሎትም ጊዜ ምስጋናን የሚጀምሩ አለቃው የአሳፍ ልጅ፥ የዛብዲ ልጅ፥ የሚካ ልጅ ማታንያ፥ በወንድሞቹም መካከል ሁለተኛ የነበረ ቦቂቦቅያ፥ የኢዶትም ልጅ፥ የጌላል ልጅ፥ የሰሙዓ ልጅ አብድያ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጸሎትም ጊዜ ምስጋናን የሚቀነቅኑ አለቃው የአሳፍ ልጅ የዘብዲ ልጅ የሚካ ልጅ መታንያ፥ በወንድሞቹም መካከል ሁለተኛ የነበረ በቅበቃር፥ የኤዶታምም ልጅ የጋላል ልጅ የሳሙስ ልጅ አብድያ። |
ጽኑ ፍቅሩም ለዘለዓለም ነውና ጌታን እንዲያመሰግኑ ኤማንንና ኤዶታምን፥ በስማቸውም የተጻፉትን ተመርጠው የቀሩትን ከእነርሱ ጋር በዚያ ተዋቸው።
የሌዋውያኑ መሪዎች ሐሻብያ፥ ሼሬብያ፥ የቃድሚኤል ልጅ ኢያሱና ወንድሞቻቸው ደግሞ ከፊት ለፊታቸው ሆነው የእግዚአብሔር ሰው ዳዊት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ክፍል በክፍል ትይዩ ሆነው ያወድሱና ያመሰግኑ ነበር።
የይሁዳንም አለቆች ወደ ቅጥሩ ላይ አወጣኋቸው፥ አመስጋኞቹንም በሁለት ታላላቅ ተርታ አቆምኋቸው፥ አንዱም ወደ ቀኝ በቅጥሩ ላይ ወደ ጉድፍ መጣያው በር ሄደ።