La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ናሆም 3:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ነጋዴዎችሽን ከሰማይ ከዋክብት ይልቅ አበዛሽ፤ አንበጣ ተዘረጋና በረረ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከሰማይ ከዋክብት እስኪበልጡ ድረስ፣ የነጋዴዎችሽን ቍጥር አበዛሽ፤ ምድሪቱን ግን እንደ አንበጣ ግጠው አሟጠጡ፤ ከዚያ በርረው ሄዱ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ነጋዴዎችሽ ከሰማይ ከዋክብት ይበልጥ በዝተዋል፤ ነገር ግን እንደ አንበጣ ምድሪቱን ግጠው በረው ይሄዳሉ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ነጋዴዎችሽን ከሰማይ ከዋክብት ይልቅ አበዛሽ፣ ደጎብያ ተዘረጋ፥ በረረም።

Ver Capítulo



ናሆም 3:16
7 Referencias Cruzadas  

ወደ ሜዳም አወጣውና፦ “ወደ ሰማይ ተመልከት፥ ከዋክብትንም ልትቈጥራቸው ትችል እንደሆነ ቁጠር” አለው። ዘርህም እንደዚሁ ይሆናል አለው።


በእውነት መባረክን እባርክሃለሁ፥ ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብት እና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ አበዛዋለሁ፤ ዘሮችህም የጠላቶችን ደጅ ይወርሳሉ፥


ልጆቻቸውን እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛህ፥ እንዲገቡና እንዲወርሷት ለአባቶቻቸው ወደ ነገርሃቸው ምድር አገባሃቸው።


ተናገረ፥ አንበጣም ስፍር ቍጥር የሌለውም ኩብኩባ መጣ፥


አክሊል በተቀዳጀች፥ ነጋዴዎችዋ መሳፍንት በሆኑ፥ በምድር የከበሩ ሻጮችና ለዋጮች በነበሯት፥ በጢሮስ ላይ ይህን ያሰበ ማን ነበር?


የሰማይን ሠራዊት መቁጠር የባሕርንም አሸዋ መስፈር እንደማይቻል፥ እንዲሁ የባርያዬን የዳዊትን ዘርና የሚያገለግሉኝን ሌዋውያንን አበዛለሁ።”


ከተምች የቀረውን አንበጣ በላው፥ ከአንበጣም የቀረውን ደጎብያ በላው፥ ከደጎብያም የቀረውን ኩብኩባ በላው።