እግዚአብሔር ኖኅንና ከእርሱ ጋር በመርከቡ ውስጥ የነበሩትን አራዊትና እንስሶች ሁሉ አሰበ። ነፋስ በምድር ላይ እንዲነፍስ አደረገ፥ ውኃውም ጎደለ፥
ናሆም 1:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባሕሩንም ይገሥጻል፥ ያደርቀዋልም፥ ወንዞችን ሁሉ ያደርቃል፤ ባሳንና ቀርሜሎስም ጠውልጎአል፥ የሊባኖስም አበባ ጠውልጎአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባሕርን ይገሥጻል፤ ያደርቀዋልም፤ ወንዞችን ሁሉ ያደርቃል። ባሳንና ቀርሜሎስ ጠውልገዋል፤ የሊባኖስም አበቦች ረግፈዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ባሕሩንና ወንዞቹን ገሥጾ ያደርቃቸዋል። በባሳንና በቀርሜሎስ የሚገኙ ዕፀዋት ይደርቃሉ፤ የሊባኖስም አበቦች ይጠወልጋሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባሕሩንም ይገሥጻታል፥ ያደርቃትማል፥ ወንዞችንም ሁሉ ያደርቃል፣ ባሳንና ቀርሜሎስም ላልተዋል፥ የሊባኖስም አበባ ጠውልጎአል። |
እግዚአብሔር ኖኅንና ከእርሱ ጋር በመርከቡ ውስጥ የነበሩትን አራዊትና እንስሶች ሁሉ አሰበ። ነፋስ በምድር ላይ እንዲነፍስ አደረገ፥ ውኃውም ጎደለ፥
የባሕር ዓሣዎች፥ የሰማይ ወፎች፥ የምድር አራዊት፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱ ተንቀሳቃሾች ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ በፊቴ ይንቀጠቀጣሉ፥ ተራሮች ይገለባበጣሉ፥ ገደሎች ይወድቃሉ፥ ቅጥርም ሁሉ ወደ ምድር ይወድቃል።
እንዲህም አለ፦ “ጌታ በጽዮን ሆኖ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይጮኻል፥ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ድምፁን ያስተጋባል፤ የእረኞችም ማሰማርያዎች ይጠወልጋሉ፥ የቀርሜሎስም ራስ ይደርቃል።”
ሰባቱን ከዋክብትና ኦሪዮን የተባለውን ኮበብ የፈጠረ፥ የሞትን ጥላ ወደ ንጋት የሚለውጥ፥ ቀኑንም በሌሊት የሚያጨልም፥ የባሕሩንም ውኆች ጠርቶ በምድር ፊት ላይ የሚያፈስሳቸው እርሱ፥ ስሙ ጌታ ነው።
ከላይ የሚወርደው ውኃ ቆመ፤ በጻርታን አጠገብ ባለችው አዳም በምትባል ከተማ በሩቅ ቆሞ በአንድ ክምር ተነሣ፤ ወደ ዓረባ ባሕር ወደ ጨው ባሕር የሚወርደው ውኃ ፈጽሞ ተቋረጠ፤ ሕዝቡም በኢያሪኮ ፊት ለፊት ተሻገሩ።