Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 42:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ተራሮችንና ኮረብቶችን አፈርሳለሁ፥ ቡቃያዎቻቸውንም ሁሉ አደርቃለሁ፤ ወንዞችንም ደሴቶች አደርጋለሁ፥ ኩሬዎችንም አደርቃለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ተራራውንና ኰረብታውን አፈርሳለሁ፤ ዕፀዋቱን ሁሉ አደርቃለሁ፤ ወንዙንም ደሴት አደርጋለሁ፤ ኵሬውን አደርቃለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ተራራዎችንና ኰረብቶችን አጠፋለሁ፤ በእነርሱ ላይ የበቀሉትን ሁሉ አደርቃለሁ፤ ወንዞችን ወደ ደረቅ ምድር እለውጣለሁ፤ ኩሬዎችንም አደርቃለሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ተራ​ሮ​ች​ንና ኮረ​ብ​ቶ​ችን አፈ​ር​ሳ​ለሁ፤ ቡቃ​ያ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሁሉ አደ​ር​ቃ​ለሁ፤ ወን​ዞ​ች​ንም ደሴ​ቶች አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ኩሬ​ዎ​ች​ንም አደ​ር​ቃ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ተራሮችንና ኮረብቶችን አፈርሳለሁ፥ ቡቃያዎቻቸውንም ሁሉ አደርቃለሁ፥ ወንዞችንም ደሴቶች አደርጋለሁ፥ ኵሬዎችንም አደርቃለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 42:15
22 Referencias Cruzadas  

በጨነቀኝ ጊዜ ጌታን ጠራሁት፥ ወደ አምላኬም ጮኽሁ፥ ከመቅደሱም ቃሌን ሰማኝ፥ ጩኸቴም በፊቱ ወደ ጆሮው ገባ።


እነሆ፥ እንደ ተሳለች እንደ አዲስ ባለ ጥርስ ማሄጃ አድርጌሃለሁ፤ ተራሮችንም ታሄዳለህ ታደቅቃቸውማለህ፥ ኮረብቶችንም እንደ ገለባ ታደርጋቸዋለህ።


ቀላዩም፦ “ደረቅ ሁን፥ ፈሳሾችህንም አደርቃለሁ” እላለሁ፤


ተራሮቼንም ሁሉ መንገድ አደርጋለሁ፥


በመጣሁስ ጊዜ ሰው ስለምን አልነበረም? በጠራሁስ ጊዜ የሚመልስ ስለምን አልነበረም? መታደግ እንዳትችል እጄ አጭር ሆናለችን? ወይስ ለማዳን ኃይል የለኝም? እነሆ፥ በገሠጽሁ ጊዜ ባሕርን አደርቃለሁ፥ ወንዞችንም ምድረ በዳ አደርጋቸዋለሁ፤ ውኃም አጥተው ዓሦቻቸው ይገማሉ፥ በጥማትም ይሞታሉ።


ተራሮችን አየሁ፥ እነሆም፥ ተንቀጠቀጡ፥ ኮረብቶችም ሁሉ ተናወጡ።


በቅንዓቴና በቁጣዬ እሳት ተናግሬአለሁ፦ በዚያ ቀን በእስራኤል ምድር ጽኑ መናወጥ ይሆናል፤


የባሕር ዓሣዎች፥ የሰማይ ወፎች፥ የምድር አራዊት፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱ ተንቀሳቃሾች ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ በፊቴ ይንቀጠቀጣሉ፥ ተራሮች ይገለባበጣሉ፥ ገደሎች ይወድቃሉ፥ ቅጥርም ሁሉ ወደ ምድር ይወድቃል።


የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላልና፦ እንደገና በቅርብ ጊዜ ሰማያትንና ምድርን ባሕርንና የብስን አናውጣለሁ፤


እርሱም በጭንቅ ባሕር ያልፋል፥ የባሕር ሞገድም ጸጥ ያሰኛል፥ የዐባይም ወንዝ ከጥልቀት ይደርቃል። የአሦርም ትዕቢት ይዋረዳል፥ የግብጽም በትረ መንግሥት ይጠፋል።


በዚያም ሰዓት ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ከከተማይቱም ዐሥረኛው እጅ ወደቀ፤ በመናወጥም ሰባት ሺህ ሰዎች ተገደሉ፤ የቀሩትንም ፍርሃት ያዛቸው፤ ለሰማዩም አምላክ ክብር ሰጡ።


ስድስተኛውም መልአክ ጽዋውን በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ ላይ አፈሰሰ፤ ከፀሐይም መውጫ ለሚመጡ ነገሥታት መንገድ እንዲሰናዳላቸው ውሃው ደረቀ።


መብረቅና ድምጽም ነጎድጓድም ሆኑ፤ ትልቅም የምድር መናወጥ ሆነ፤ ሰው በምድር ከተፈጠረ ጀምሮ እንዲህ ያለ ታላቅ መናውጥ ከቶ አልነበረም፤ ነውጡ እጅግ ትልቅ ነበር።


ታላቅና ነጭ ዙፋን፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠውን አየሁ፤ ምድርና ሰማይም ከፊቱ ሸሹ፤ ስፍራም አልተገኘላቸውም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos