ሚክያስ 6:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምን ይዤ ወደ ጌታ ፊት ልቅረብ፥ በልዑል አምላክ ፊት ልስገድን? የሚቃጠል መሥዋዕትና የአንድ ዓመት ጥጃ ይዤ በፊቱ ልቅረብን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምን ይዤ በእግዚአብሔር ፊት ልቅረብ፣ በልዑል አምላክ ፊት ልስገድ? የሚቃጠለውን መሥዋዕት፣ ከአንድ ዓመት ጥጃ ጋራ ይዤ በፊቱ ልቅረብን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለኀያሉ አምላክ ለእግዚአብሔር ለመስገድ በምመጣበት ጊዜ ምን ይዤ ልቅረብ? ለእርሱ የሚቃጠል መሥዋዕት ይሆኑ ዘንድ የአንድ ዓመት ጥጆችን ይዤ ልምጣን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምን ይዤ ወደ እግዚአብሔር ፊት ልምጣና በልዑል አምላክ ፊት ልስገድ? የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንዱን ዓመት ጥጃ ይዤ በፊቱ ልምጣን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምን ይዤ ወደ እግዚአብሔር ፊት ልምጣና በልዑል አምላክ ፊት ልስገድ? የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንዱን ዓመት ጥጃ ይዤ በፊቱ ልምጣን? |
የቂጣውን በዓል ጠብቅ፤ በተመደበው በአቢብ ወር ሰባት ቀን ያልቦካ ቂጣ እንዳዘዝሁህ ትበላለህ፤ በዚህ ወር ከግብጽ ምድር ወጥታችኋልና፥ በፊቴም ባዶ እጃችሁን አትታዩ።
ስለ ምንስ ከሳባ ዕጣንን፥ ከሩቅም አገር የከበረውንም ዘይት ታመጡልኛላችሁ? የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን አልቀበለውም፥ ሌላ መሥዋዕታችሁም ደስ አያሰኘኝም።
የምድሪቱ ሕዝብ ግን በየክብረ በዓሉ ቀን ወደ ጌታ ፊት በመጡ ጊዜ በሰሜን በር በኩል ሊሰግድ የገባው በደቡብ በር በኩል ይውጣ፥ በደቡብ በር የገባው በሰሜን በር በኩል ይውጣ፤ በፊት ለፊት ባለው ይውጣ እንጂ በገባበት በር አይመለስ።
የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁና የእህሉን ቁርባናችሁን ብታቀርቡልኝም እንኳ አልቀበለውም፤ ለአንድነት መሥዋዕት የምታቀርቡልኝን የሰቡትን እንስሶች አልመለከትም።
እርሱን በፍጹም ልብህ፥ በፍጹም አእምሮህ፥ በፍጹም ነፍስህ፥ በፍጹም ኋይልህ መውደድ፥ እንዲሁም ጐረቤትህን እንደ ራስህ መውደድ ከሚቃጠል መሥዋዕት ሁሉና ከሌሎችም መሥዋዕቶች ይበልጣል።”
ኢየሱስም መልሶ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ የምትፈልጉኝ እንጀራን ስለ በላችሁና ስለ ጠገባችሁ ነው እንጂ ምልክቶችን ስላያችሁ አይደለም።
ሳሙኤልም፦ “ጌታ ለቃሉ በመታዘዝ ደስ የሚለውን ያህል፥ ጌታ፥ በሚቃጠል ቁርባንና መሥዋዕት ደስ ይለዋልን? እነሆ! መታዘዝ ከመሥዋዕት፥ ማዳመጥም ከአውራ በግ ሥብ ይበልጣል።