ሚክያስ 5:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም ሰላም ይሆናል፤ አሦር ወደ ምድራችን ከመጣ፥ ምሽጎቻችንንም ከረገጠ፥ ሰባት እረኞችና ስምንት አለቆች እናስነሣበታለን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእግዚአብሔር ኀይል፣ በአምላኩ በእግዚአብሔር ስም ታላቅነት፣ ጸንቶ ይቆማል፤ መንጋውንም ይጠብቃል። በዚያ ጊዜ ኀያልነቱ እስከ ምድር ዳርቻ ስለሚደርስ፣ ተደላድለው ይኖራሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ በእግዚአብሔር ኀይል ተነሥቶ የበግ መንጋውን ያሰማራል፤ ይህንንም የሚያደርገው በግርማዊው በእግዚአብሔር በአምላኩ ስም ነው፤ እርሱ አሁን እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ታላቅ ስለሚሆን እነርሱ ያለ ስጋት ይኖራሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም ይቆማል፥ በእግዚአብሔርም ኃይል በአምላኩ በእግዚአብሔር ስም ግርማ መንጋውን ይጠብቃል፥ እነርሱም ይኖራሉ፥ እርሱ አሁን እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ታላቅ ይሆናልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ይቆማል፥ በእግዚአብሔርም ኃይል በአምላኩ በእግዚአብሔር ስም ግርማ መንጋውን ይጠብቃል፥ እነርሱም ይኖራሉ፥ እርሱ አሁን እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ታላቅ ይሆናልና። |
አሁንም ከማኅፀን ጀምሮ በሠራኝ በጌታ ዐይን ከብሬአለሁና፥ አምላኬም ጉልበት ሆኖኛልና ያዕቆብን ወደ እርሱ እንድመልስ እስራኤልንም ወደ እርሱ እንድሰበስብ አገልጋዩ አድርጎኝ ጌታ እንዲህ ይላል።
ስለዚህ ጌታ ታላቁንና ብርቱውን የጐርፍ ውሃ፤ የአሦርን ንጉሥ ከነግርማ ሞገሱ ሁሉ ያመጣባቸዋል። ውሃውም ከቦዩ ዐልፎ ተርፎ በወንዙ ዳር ያለውን ምድር ሁሉ ያጥለቀልቃል፤
በአትክልት ቦታ መካከል ባለው ጥሻ ብቻቸውን የተቀመጡት የርስትህን መንጋ፥ ሕዝብህን በበትርህ ጠብቅ፤ እንደ ቀደመው ዘመን በበሳንና በገለዓድ ይሰማሩ።
ሰይፍ ሆይ፥ ባልንጀራዬ በሆነው ሰው በእረኛዬ ላይ ንቃ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ፤ በጎቹም እንዲበተኑ እረኛውን ምታ፤ እጄንም በታናናሾች ላይ አዞራለሁ።
ሠረገላውንም ከኤፍሬም፥ ፈረሱንም ከኢየሩሳሌም አጠፋለሁ፤ የሰልፉም ቀስት ይሰበራል፥ ለአሕዛብም ሰላምን ይናገራል፤ ግዛቱም ከባሕር እስከ ባሕር፥ ከወንዙም እስከ ምድር ዳርቻ ድርስ ይሆናል።
ኢየሱስም “ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ ‘እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዐርጋለሁ፤’ ብለሽ ንገሪአቸው፤” አላት።
ሰባተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በሰማይም እንዲህ የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ተሰሙ፦ “የዓለም መንግሥት የጌታችንና የመሢሑ ሆነች፤ ለዘለዓለምም እስከ ዘለዓለም ይነግሣል፤”