Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ማቴዎስ 2:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 “በይሁዳ ምድር የምትገኚ አንቺ ቤተልሔም፥ ከይሁዳ ገዢዎች ከቶ አታንሽም፤ ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ መሪ ከአንቺ ይወጣልና።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 “ ‘በይሁዳ ምድር የምትገኚው አንቺ ቤተ ልሔም፣ ከሌሎቹ ከይሁዳ ገዦች በምንም አታንሺም፤ የሕዝቤ የእስራኤል ጠባቂ የሚሆን፣ ከአንቺ ይወጣልና።’ ”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ‘በይሁዳ ክፍለ ሀገር የምትገኚ አንቺ ቤተልሔም ሆይ! ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ መሪ ከአንቺ ስለሚወጣ፥ ከይሁዳ ታላላቅ ከተሞች በምንም አታንሺም።’ ”

Ver Capítulo Copiar




ማቴዎስ 2:6
24 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ ወላጂቱ እስከምትወልድበት ጊዜ ድረስ አሳልፎ ይሰጣቸዋል፤ ከዚህ በኋላ የቀሩት ወንድሞቹ ወደ እስራኤል ልጆች ይመለሳሉ።


ክርስቶስ ከዳዊት ዘር፥ ዳዊትም ከነበረባት መንደር ከቤተልሔም እንደሚመጣ መጽሐፍ አልተናገረምን?”


በትረ መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም፥ የገዥም ዘንግ ከእግሮቹ መካከል፥ ገዥ የሆነው እስኪመጣ ድረስ፥ የአሕዛብ መታዘዝም ለእርሱ ይሆናል።


ሰባተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በሰማይም እንዲህ የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ተሰሙ፦ “የዓለም መንግሥት የጌታችንና የመሢሑ ሆነች፤ ለዘለዓለምም እስከ ዘለዓለም ይነግሣል፤”


ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ አላቸው “ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጥቶኛል።


መንጋውን እንደ እረኛ ያሰማራል፥ ጠቦቶቹን በክንዱ ሰብስቦ በብብቱ ይሸከማል፥ የሚያጠቡትንም በቀስታ ይመራል።


እንደ ትላንትና እንዳለፉት ሦስት ቀናት ሳኦል በእኛ ላይ ነግሦ በነበረ ጊዜ፥ እስራኤልን በጦርነት የምትመራቸው አንተ ነበርህ፤ ጌታም፥ ‘ሕዝቤን እስራኤልን ትጠብቃለህ፤ መሪያቸውም ትሆናለህ’ ብሎህ ነበር።”


እርሱም አካሉ የሆነችው የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው፤ እርሱ በሁሉ ነገር ቀዳሚ በመሆን መጀመሪያ ነው፤ ከሙታንም በኩር ነው።


ኢየሱስም በይሁዳ ቤተልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰብአ ሰገል ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፥


ሁሉንም ከእግሩ በታች አስገዛለት፤ ከሁሉ በላይም ራስ እንዲሆን ለቤተ ክርስቲያን ሰጠው።


ይሁዳም በወንድሞቹ መካከል በረታ፥ አለቃም ከእርሱ ሆነ፤ ብኩርናው ግን ለዮሴፍ ነበረ።


ከያዕቆብም የሚወጣ ገዥ ይሆናል፥ ከከተማውም በሕይወት የተረፉትን ያጠፋል።”


ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ! ትወደኛለህን?” አለው። “አዎን ጌታ ሆይ! እንደምወድህ አንተ ታውቃለህ” አለው። ኢየሱስም “ጠቦቶቼን ጠብቅ፤” አለው።


የቤተልሔም ልጆች፥ መቶ ሀያ ሦስት።


ጌታችን ከይሁዳ ነገድ እንደ ወጣ የታወቀ ነው፤ ከዚያ ነገድ ጋር በተገናኘ ስለ ካህናት ሙሴ ምንም አልተናገረም።


በዙፋኑ መካከል ያለው በጉ እረኛቸው ይሆናልና፤ ወደ ሕይወትም ውሃ ምንጭ ይመራቸዋልና፤ እግዚአብሔርም እንባዎችን ሁሉ ከዐይናቸው ያብሳል።”


የቤተልሔም አባት ሰልሞን፥ የቤት-ጋዴር አባት ሐሬፍ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios