ሚልክያስ 2:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሁላችን አባት አንድ አይደለምን? የፈጠረንስ አንድ አምላክ አይደለምን? የአባቶቻችንን ቃል ኪዳን ለማርከስ ሁላችንም ለምን ወንድማችንን እናታልላለን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁላችን አንድ አባት ያለን አይደለንምን? የፈጠረንስ አንድ አምላክ አይደለምን? ታዲያ እርስ በርሳችን ታማኝነት በማጕደል የአባቶቻችንን ኪዳን ለምን እናረክሳለን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለሁላችንም አንድ አባት ያለን አይደለምን፤ የፈጠረንስ አንድ አምላክ አይደለምን? ታዲያ ለምን የቀድሞ አባቶቻችንን ቃል ኪዳን በማፍረስ እርስ በርሳችን እምነተቢሶች እንሆናለን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሁላችን አንድ አባት ያለን አይደለምን? አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን? የአባቶቻችንን ቃል ኪዳን ለማስነቀፍ እኛ እያንዳዳችን ወንድማችንን ስለ ምን አታለልን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለሁላችን አንድ አባት ያለን አይደለምን? አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን? የአባቶቻችንን ቃል ኪዳን ለማስነቀፍ እኛ እያንዳዳችን ወንድማችንን ስለ ምን አታለልን? |
ሙሴም መጣ ለሕዝቡም የጌታ ቃሎች ሁሉ ሥርዓቱንም ሁሉ ነገረ፤ ሕዝቡም ሁሉ በአንድ ድምፅ፦ “ጌታ የተናገራቸውን ቃሎች ሁሉ እናደርጋለን” ብለው መለሱ።
አሁንም ያዕቆብ ሆይ፥ የፈጠረህ፥ እስራኤልም ሆይ፥ የሠራህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤ በስምህም ጠርቼሃለሁ፥ አንተ የእኔ ነህ።
በልቅሶ ይወጣሉ፤ እኔንም በመማፀናቸው እየመራሁ እመልሳቸዋለሁ፤ በወንዝ ዳር በቅን መንገድ አስኬዳቸዋለሁ፤ በእርሱም አይሰናከሉም፤ እኔ ለእስራኤል አባት ነኝና፥ ኤፍሬምም በኩሬ ነውና።
የሰው ልጅ ሆይ፥ በእስራኤል ምድር ባሉ ፍርስራሽ ስፍራዎች የሚኖሩ፦ አብርሃም ብቻውን ሳለ ምድሪቱን ወረሰ፤ እኛ ደግሞ ብዙዎች ነን ምድሪቱም ርስት ሆና ለእኛ ተሰጥታለች ይላሉ።
“ስሜን የምትንቁ ካህናት ሆይ፥ ልጅ አባቱን፥ ባርያም ጌታውን ያከብራል፥ እኔ አባት ከሆንሁ መከበሬ የት አለ? ጌታስ ከሆንሁ መፈራቴ ወዴት አለ?” ይላችኋል የሠራዊት ጌታ። እናንተም፦ “ስምህን የናቅነው እንዴት ነው?” ብላችኋል።
ይሁዳ አታልሎአል፥ በእስራኤልና በኢየሩሳሌም ውስጥ ርኩሰት ሠርቷል፤ ይሁዳ ጌታ የወደደውን መቅደስ አርክሶአል፥ የባዕድንም አምላክ ልጅ አግብቶአል።
ደቀ መዛሙርታቸውን ከሄሮድስ ሰዎች ጋር ላኩበት፤ እነርሱም እንዱህ አሉት “መምህር ሆይ! እውነተኛ እንደሆንህ የእግዚአብሔርንም መንገድ በእውነት እንደምታስተምር እናውቃለን፤ ለማንምም አታደላም፤ የሰውን ፊት አታይምና፤
እንግዲህ ለንስሓ የሚገቡ ፍሬዎች አፍሩ፤ በልባችሁም ‘አብርሃም አባት አለን፤’ አትበሉ፤ ከእነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ሊያስነሣለት እግዚአብሔር እንደሚችል እነግራችኋለሁና።
እናንተ የአባታችሁን ሥራ ትሠራላችሁ፤” አላቸው። እነርሱም “እኛስ ከዝሙት አልተወለድንም፤ አንድ አባት አለን፤ እርሱም እግዚአብሔር ነው፤” አሉት።
ምናልባትም እየመረመሩ ያገኙት እንደሆነ፥ እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩ የሰውን ወገኖች ሁሉ ከአንድ ፈጠረ፤ የተወሰኑትንም ዘመኖችና ለሚኖሩበት ስፍራ ዳርቻ መደበላቸው። ቢሆንም ከእያንዳንዳችን የራቀ አይደለም።
በማግሥቱም እርስ በርሳቸው ሲጣሉ አገኛቸው፤ ሊያስታርቃቸውም ወዶ ‘ሰዎች ሆይ! እናንተስ ወንድማማች ናችሁ፤ ስለምን እርስ በርሳችሁ ትበዳደላላችሁ?’ አላቸው።
ለእኛስ ነገር ሁሉ ከእርሱ የሆነ እኛም ለእርሱ የሆንን አንድ እግዚአብሔር አብ አለን፤ እንዲሁም ነገር ሁሉ በእርሱ በኩል የሆነ እኛም በእርሱ በኩል የሆንን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አለን።
አስቀድመን ደግሞ እንደ ነገርናችሁና እንደ መሰከርንላችሁ፥ ጌታ ስለዚህ ነገር ሁሉ የሚበቀል ነውና፥ ማንም በዚህ ነገር አይተላለፍ፤ ወንድሙንም አያታልል።
ከዚህም በተጨማሪ የቀጡን የሥጋችን አባቶች ነበሩን፤ እናከብራቸውም ነበር፤ ታዲያ እንዴት በላቀ ለመናፍስት አባት አብልጠን ልንገዛና በሕይወት ልንኖር አይገባንም?