Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዕብራውያን 12:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ከዚህም በተጨማሪ የቀጡን የሥጋችን አባቶች ነበሩን፤ እናከብራቸውም ነበር፤ ታዲያ እንዴት በላቀ ለመናፍስት አባት አብልጠን ልንገዛና በሕይወት ልንኖር አይገባንም?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ከዚህም በላይ፣ እኛ ሁላችን የሚቀጡን ምድራዊ አባቶች ነበሩን፤ እናከብራቸውም ነበር። ታዲያ ለመናፍስት አባት እንዴት አብልጠን በመገዛት በሕይወት አንኖርም!

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ከዚህም በቀር እኛ ሁላችን የሚቀጡን የሥጋ አባቶች ነበሩን፤ እናከብራቸውም ነበር፤ ታዲያ፥ በሕይወት ለመኖር ለመንፈሳዊ አባታችን በይበልጥ መታዘዝ እንዴት አይገባንም!

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 በሥጋ የወ​ለ​ዱን አባ​ቶ​ቻ​ችን የሚ​ቀ​ጡን፥ እኛም የም​ን​ፈ​ራ​ቸው ከሆነ፥ እን​ግ​ዲያ ይል​ቁን ለመ​ን​ፈስ አባ​ታ​ችን ልን​ታ​ዘ​ዝና ልን​ገዛ በሕ​ይ​ወ​ትም ልን​ኖር እን​ዴት ይገ​ባን ይሆን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ከዚህም በላይ የቀጡን የሥጋችን አባቶች ነበሩን እናፍራቸውም ነበር፤ እንዴትስ ይልቅ ለመናፍስት አባት አብልጠን ልንገዛና በሕይወት ልንኖር በተገባን?

Ver Capítulo Copiar




ዕብራውያን 12:9
28 Referencias Cruzadas  

እነርሱም በግምባራቸው ወድቀው በመስገድ እንዲህ አሉ፦ “አምላክ ሆይ! አንተ የሥጋ ለባሽ ሁሉ መንፈስ አምላክ፥ አንድ ሰው ኃጢአት ቢሠራ አንተ በማኅበሩ ሁሉ ላይ ትቈጣለህን?”


የሥጋ ለባሽ ሁሉ መንፈስ አምላክ የሆነ ጌታ በማኅበሩ ላይ አንድ ሰው ይሹም።


ሰማያትን የፈጠረ የዘረጋቸውም፥ ምድርንና በውስጥዋ ያለውን ያጸና፥ በእርሷ ላይ ለሚኖሩ ሕዝብ እስትንፋስን፥ ለሚሄዱባትም መንፈስን የሚሰጥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦


ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፤ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው።


የሕያዋን ሁሉ ነፍስ የሰውም ሁሉ እስትንፋስ በእጁ ናት።


ስለ እስራኤል የተነገረ የጌታ ቃል ይህ ነው። ሰማያትን የዘረጋ፥ ምድርንም የመሠረተ፥ የሰውንም መንፈስ በውስጡ የሠራ ጌታ እንዲህ ይላል፦


“ጌታ አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም፥ አባትህንና እናትህን አክብር።


“ጌታ ሆይ፥ በዚህ ነገር ሰዎች በሕይወት ይኖራሉ፥ በዚህም ሁሉ የመንፈሴ ሕይወት ነው፤ አንተም ፈወስከኝ ወደ ሕይወትም መለስከኝ።


እንግዲህ እግዚአብሔር በወሰነው ጊዜ ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከእግዚአብሔር ብርቱ እጅ ሥር ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ።


እንግዲህ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አስገዙ፤ ዲያብሎስን ተቃወሙት፤ ከእናንተም ይሸሻል።


መንፈስም የፈጠርሁትም ነፍስ ከፊቴ እንዳይዝል ለዘለዓለም አልጣላም፥ ሁልጊዜም አልቈጣም።


ከእናንተ እያንዳንዱ ሰው እናቱንና አባቱን ያክብር፥ ሰንበታቴንም ጠብቁ፥ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ።


አባቶችም የእነርሱ ናቸው፤ ከእነርሱም ዘር ክርስቶስ በሥጋ መጣ፤ እርሱም ከሁሉ በላይ የሆነ ለዘለዓለም የተባረከ አምላክ ነው፤ አሜን።


በአባትዋ የምታላግጥን የእናትዋንም ትእዛዝ የምትንቅን ዐይን የሸለቆ ቁራዎች ይጐጠጉጡአታል፥ አሞራዎችም ይበሉአታል።


“‘አባቱን ወይም እናቱን የሚያቃልል የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ፥ ‘አሜን!’ ይበል።


አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ፥ ነፍስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ።


በጌታ ፊት ራሳችሁን አዋርዱ፥ እርሱም ከፍ ከፍ ያደርጋችኋል።


“ስሜን የምትንቁ ካህናት ሆይ፥ ልጅ አባቱን፥ ባርያም ጌታውን ያከብራል፥ እኔ አባት ከሆንሁ መከበሬ የት አለ? ጌታስ ከሆንሁ መፈራቴ ወዴት አለ?” ይላችኋል የሠራዊት ጌታ። እናንተም፦ “ስምህን የናቅነው እንዴት ነው?” ብላችኋል።


አባትንና እናትን አቃለሉ፥ በመካከልሽ መጻተኛውን ጨቆኑ፥ በአንቺ ውስጥ የሙት ልጅንና መበለቲቱን አስጨነቁ።


ስለ ሥጋ ዘመዶቼና ስለ ወንድሞቼ ስል እኔ ራሴ ከክርስቶስ ተለይቼ የተረገምሁ እንድሆን እመኝ ነበር።


ወንጌሉም ስለ ልጁ፥ በሥጋ ከዳዊት ዘር እንደመጣ፥


ነቢይ ስለ ሆነ፥ ከወገቡም ፍሬ በዙፋኑ ያስቀምጥ ዘንድ እግዚአብሔር መሐላ እንደማለለት ስለ አወቀ፥


እንዲህም አለ፦ “በአንዲት ከተማ እግዚአብሔርን የማይፈራ ሰውንም የማያፍር አንድ ዳኛ ነበረ።


ለአያሌ ቀናትም ሊፈርድላት አልፈለገም ነበር፤ ከዚህ በኋላ ግን በልቡ ‘ምንም እግዚአብሔርን ባልፈራ ሰውንም ባላፍር፥


እርሱም እንዲህ አለኝ፦ “እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛዎች ናቸው፤ የነቢያትም መናፍስት ጌታ አምላክ በቶሎ ሊሆን የሚገባውን ነገር ለባርያዎቹ እንዲያሳይ መልአኩን ሰደደ።”


አባትን፦ ምን ወልደሃል? ወይም ሴትን፦ ምን አማጥሽ? ለሚል ወዮ!


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios