ሉቃስ 1:69 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአገልጋዩ በዳዊት ቤት የመዳን ቀንድን አስነስቶልናል፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በብላቴናው በዳዊት ቤት፣ የድነት ቀንድ አስነሥቶልናል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከአገልጋዩ ከዳዊት ዘር ኀያል አዳኝ አስነሥቶልናል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከባርያው ከዳዊት ቤት የምንድንበትን ቀንድ አስነሣልን፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከጥንት ጀምሮ በነበሩት በቅዱሳን ነቢያት አፍ እንደ ተናገረ፥ በብላቴናው በዳዊት ቤት የመዳን ቀንድን አስነስቶልናል፤ |
ስለዚህ ስምህ ለዘለዓለም ታላቅ ይሆናል፤ ‘የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የእስራኤል አምላክ ነው!’ ይባላል። የአገልጋይህ የዳዊትም ቤት በፊትህ የጸና ይሆናል።
ከልጅህም ቢሆን መንግሥቱን በሙሉ አልወስድበትም፤ ለአገልጋዬ ለዳዊትና ለራሴ ርስት እንድትሆን ለመረጥኳት ለኢየሩሳሌም ከተማ ስል አንድ ነገድ እተውለታለሁ።”
“በዚያ ቀን የወደቀችውን የዳዊትን ድንኳን አነሣለሁ፥ የተናደውንም ቅጥርዋን እጠግናለሁ፤ የፈረሰውንም አድሳለሁ፥ እንደ ቀደመውም ዘመን እሠራታለሁ፤
“እኔ ኢየሱስ በአብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ይህን እንዲመሰክርላችሁ መልአኬን ላክሁ። እኔ የዳዊት ሥርና ዘር ነኝ፤ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ።”
ሐናም እንዲህ ብላ ጸለየች፦ “ልቤ በጌታ ደስ ይለዋል፥ ቀንዴም በጌታ ከፍ ከፍ ብሏል፤ በማዳንህ ደስ ብሎኛልና፥ አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ።
ጌታ! እርሱን የሚቃወሙ ይደቅቃሉ፥ ከሰማይም ያንጐደጉድባቸዋል፥ ጌታ እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል፥ ለንጉሡም ኃይል ይሰጣል፥ የመሢሑንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል።”