ዘሌዋውያን 7:38 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ በሲና ምድረ በዳ ቁርባናቸውን ለጌታ እንዲያቀርቡ ለእስራኤል ልጆች ባዘዘ ጊዜ በሲና ተራራ ለሙሴ ያዘዘው ይህ ነው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም፣ በሲና ምድረ በዳ እስራኤላውያን መሥዋዕታቸውን ለእግዚአብሔር እንዲያቀርቡ ባዘዛቸው ቀን በሲና ተራራ ላይ ለሙሴ የሰጠው ሥርዐት ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም በረሓ በሆነው በሲና ተራራ እስራኤላውያን መሥዋዕት እንዲያቀርቡ ባዘዛቸው በዚያ ቀን እግዚአብሔር ለሙሴ እነዚህን ትእዛዞች ሰጠው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር በሲና ምድረ በዳ ቍርባናቸውን በእግዚአብሔር ፊት ያቀርቡ ዘንድ ለእስራኤል ልጆች ባዘዘ ጊዜ በሲና ተራራ ለሙሴ ያዘዘው ይህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር በሲና ምድረ በዳ ቁርባናቸውን ለእግዚአብሔር ያቀርቡ ዘንድ ለእስራኤል ልጆች ባዘዘ ጊዜ በሲና ተራራ ለሙሴ ያዘዘው ይህ ነው። |