Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘሌዋውያን 26:46 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

46 ጌታም በእርሱና በእስራኤል ልጆች መካከል በሲና ተራራ ላይ በሙሴ እጅ የሰጣቸው ሥርዓቶችና ፍርዶች ሕግጋትም እነዚህ ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

46 እግዚአብሔር በራሱና በእስራኤላውያን መካከል በሲና ተራራ ላይ በሙሴ በኩል ያቆማቸው ሥርዐቶች፣ ሕጎችና ደንቦች እነዚህ ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

46 እግዚአብሔር በእርሱና በእስራኤል ሕዝብ መካከል በሙሴ አማካይነት በሲና ተራራ ላይ የሰጣቸው ደንቦች፥ ሥርዓቶችና ሕጎች እነዚህ ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

46 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ር​ሱና በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል በሲና ተራራ ላይ በሙሴ እጅ የሰ​ጣ​ቸው ሥር​ዐ​ቶ​ችና ፍር​ዶች፥ ሕግ​ጋ​ትም እነ​ዚህ ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

46 እግዚአብሔርም በእርሱና በእስራኤል ልጆች መካከል በሲና ተራራ ላይ በሙሴ እጅ ያደረጋቸው ሥርዓቶችና ፍርዶች ሕግጋትም እነዚህ ናቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 26:46
15 Referencias Cruzadas  

ጌታ በሲና ተራራ ላይ ለእስራኤል ልጆች ሙሴን ያዘዘው ትእዛዛት እነዚህ ናቸው።


“የአባቶቻችሁ አምላክ ጌታ፥ እንድትወርሷት በሰጣችሁ ምድር ላይ በምትኖሩበት ጊዜ ሁሉ፥ በጥንቃቄ ልትከተሏቸው የሚገባችሁ ሥርዓቶችና ሕጎች እነዚህ ናቸው።


“ጌታ አምላክህ በርስትነት በሚሰጥህ ምድር እንድትጠብቃት እንዳስተምርህ ያዘዘኝ ትእዛዝ፥ ሕግና ሥርዓት ይህች ናት።


አምላካችሁን ጌታን ተከተሉት፤ ፍሩት፤ ትእዛዞቹንም ጠብቁ፤ ታዘዙት፤ አገልግሉት፤ ከእርሱም ጋር ተጣበቁ።


ጌታም ሙሴን በሲና ተራራ ላይ እንዲህ ብሎ ተናገረው፦


ሕግ በሙሴ ተሰጥቶ ነበርና፤ ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ሆነ።


መንገድህ በባሕር ውስጥ ነው፥ ያለፍከውም ኃይለኛ ውኆች በኩል ነው፤ ዱካህ ግን አልታወቀም።


ጌታ በሙሴ አንደበት እንዳዘዘ፥ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ያገለገሉት ሁሉ፥ ከቀዓታውያን ወገኖች የተቈጠሩት፥ ሙሴና አሮን የቈጠሩአቸው፥ እነዚህ ናቸው።


አሮንና ልጆቹም ጌታ በሙሴ አንደበት ያዘዘውን ቃላት ሁሉ አደረጉ።


ጌታ በሲና ምድረ በዳ ቁርባናቸውን ለጌታ እንዲያቀርቡ ለእስራኤል ልጆች ባዘዘ ጊዜ በሲና ተራራ ለሙሴ ያዘዘው ይህ ነው።”


ጌታ ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦


ጌታ በሙሴ አንደበት የእስራኤልን ልጆች በዮርዳኖስ አጠገብ በኢያሪኮ አንጻር በሞዓብ ሜዳ ያዘዛቸው ትእዛዝና ፍርድ እነዚህ ናቸው።


“እነሆ፥ እናንተ ገብታችሁ በምትወርሱአት ምድር ውስጥ እንዲህ እንድታደርጉ ጌታዬ አምላኬ እንዳዘዘኝ ሥርዓትንና ሕግጋትን አስተማርኋችሁ።


ጌታ በኮሬብ ከገባው ቃል ኪዳን በተጨማሪ በሞዓብ ምድር ከእስራኤላውያን ጋር እንዲያደርግ ሙሴን ያዘዘው የኪዳኑ ቃሎች የሚከተሉት ናቸው፦


ይህ ሙሴ የሰጠን ሕግ፥ የያዕቆብ ጉባኤ ርስት ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios