ዘሌዋውያን 7:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን የረከሰ ሰው ሆኖ ሳለ፥ ለጌታ ከሆነው ከአንድነት መሥዋዕት ሥጋ የበላ እንደሆነ፥ ያ ሰው ከሕዝቡ ተለይቶ ይጥፋ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ንጹሕ ያልሆነ ማንኛውም ሰው ለእግዚአብሔር የቀረበውን የትኛውንም የኅብረት መሥዋዕት ሥጋ ቢበላ፣ ከሕዝቡ ፈጽሞ ይወገድ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን አንድ ሰው ንጹሕ ሳይሆን የአንድነቱን መሥዋዕት ሥጋ ቢበላ ከእግዚአብሔር ሕዝብ መለየት አለበት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኀጢአት ሳለባት፥ ለእግዚአብሔር ከሆነው ከደኅንነት መሥዋዕት ሥጋ የበላች ሰውነት፥ ያች ሰውነት ከሕዝብዋ ተለይታ ትጥፋ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰውም የረከሰ ቢሆን፥ ለእግዚአብሔርም ከሆነው ከደኅንነት መሥዋዕት ሥጋ ቢበላ፥ ያ ሰው ከሕዝቡ ተለይቶ ይጥፋ። |
ስለዚህ እንዲህ በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከደም ጋር ትበላላችሁ፥ ዓይናችሁንም ወደ ጣዖቶቻችሁ ታነሣላችሁ፥ ደምንም ታፈስሳላችሁ፤ በውኑ ምድሪቱን ትወርሳላችሁን?
መቅደሴን ለማርከስ፥ የተቀደሰውንም ስሜን ለማንቋሸሽ ልጁን ለሞሌክ ሰጥቶአልና እኔ በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አጠቊርበታለሁ፥ ከሕዝቡም መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ።
የሞተውን ሰው በድን የነካ ማናቸውም ሰው ሁለመናውን ባያነጻ የጌታን ማደሪያ ያረክሳል፤ ያ ሰው ከእስራኤል ዘንድ ተለይቶ ይጠፋል፤ በእርሱም ላይ ከርኩሰት የሚያነጻ ውኃ አልተረጨምና ርኩስ ይሆናል፤ ርኩሰቱ ገና በእርሱ ላይ ነው።
ሳኦልም፥ “ዳዊት በሥርዓቱ መሠረት እንዳይነጻ የሚያደርገው አንድ ነገር ገጥሞታል፤ በእርግጥም አልነጻም” ብሎ ስላሰበ፥ በዚያ ቀን ምንም አልተናገረም።