ዘሌዋውያን 6:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለጌታ በእሳት ከሚቀረበው ቁርባን ለዘለዓለም ለልጅ ልጃችሁ ድርሻቸው እንዲሆን ከአሮን ልጆች ወንዶቹ ሁሉ ይበሉታል። የሚነካቸው ሁሉ ቅዱስ ይሆናል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማንኛውም ከአሮን ዘር የተወለደ ወንድ ሊበላው ይችላል፤ ለእግዚአብሔር ከሚቀርበው የእሳት ቍርባን ለርሱ የተመደበ የዘላለም ድርሻው ነው፤ የሚነካውም ሁሉ ቅዱስ ይሆናል።’ ” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሚመጡት ዘመናት ሁሉ ትውልዱ ከአሮን ወገን የሆነ ወንድ ሁሉ ለእግዚአብሔር ከቀረበው መባ ለእርሱ የተመደበለትን ፈንታ መብላት ይችላል፤ መባውን የሚነካ ሁሉ በቅድስናው ኀይል ይቀሠፋል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከካህናት ወገን ወንድ ሁሉ ይበላዋል፤ በዘመናችሁ ለዘለዓለም ሕግ ነው። ከሚቃጠለው የእግዚአብሔር መሥዋዕት የሚነካ ሁሉ ቅዱስ ይሆናል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእግዚአብሔር ከቀረበ ከእሳት ቍርባን ለዘላለም ለልጅ ልጃችሁ እድል ፈንታቸው እንዲሆን ከአሮን ልጆች ወንዶቹ ሁሉ ይበሉታል። የሚነካቸው ሁሉ ቅዱስ ይሆናል። |
የተቀባውም ካህን ኃጢአት ሠርቶ በሕዝቡ ላይ በደል ቢያመጣ፥ ስለ ሠራው ኃጢአቱ ነውር የሌለበት ወይፈን ለጌታ ለኃጢአት መሥዋዕት ያቀርባል።
ካህኑም ሰውነቱን ለመሸፈን የበፍታ ቀሚስና የበፍታ ሱሪ ይለብሳል፤ በመሠዊያውም ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት እሳቱ ከበላው በኋላ አመዱን አንሥቶ በመሠዊያው አጠገብ ያፈስሰዋል።
ጌታም አሮንን ተናገረው እንዲህም አለው፦ “እነሆ፥ የእስራኤል ልጆች ለእኔ የቀደሱትን እንደ ስጦታ የሚቀርበውን ቁርባኔን ሁሉ ለአንተ እንድትጠብቀው ሰጥቼሃለሁ፤ ለአንተና ለልጆችህ የክህነትህ ድርሻ እንዲሆን ለአንተ የተገባህ አድርጌ ለዘለዓለም ሰጥቼሃለሁ።
እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን አስደናቂ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ እግዚአብሔር ለራሱ ያደረጋችሁ ቅዱስ ሕዝብ ናችሁ።