ዘሌዋውያን 6:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዘወትር በመሠዊያው ላይ እሳት ይንደድ፤ እርሱም አይጥፋ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመሠዊያው ላይ ያለው እሳት ዘወትር ይንደድ፤ ምን ጊዜም አይጥፋ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እሳቱም ሳይጠፋ በመሠዊያው ላይ ሁልጊዜ ይንደድ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዘወትር በመሠዊያው ላይ እሳት ይነድዳል፤ አይጠፋም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዘወትር በመሠዊያው ላይ እሳት ይነድዳል፤ አይጠፋም። |
ከአንዱ ጠቦት ጋር አሥረኛ እጅ የኢፍ መስፈሪያ መልካም ዱቄት ከአራተኛ እጅ የኢን መስፈሪያ ተወቅጦ ከተጠለለ ዘይት ጋር የተለወሰ፥ ለመጠጥ ቁርባን የሚሆን ደግሞ አራተኛ እጅ የኢን መስፈሪያ የወይን ጠጅ ታቀርባለህ።
ወደ ሰሜን የሚመለከተው ቤት መሠዊያውን ለሚጠብቁ ካህናት ነው፤ እነዚህ ከሌዊ ልጆች መካከል እንዲያገለግሉት ወደ ጌታ የሚቀርቡ የሳዶቅ ልጆች ናቸው።”
እሳቱም በመሠዊያው ላይ ዘወትር ይንደድበት፥ አይጥፋም፤ ካህኑም ማለዳ ማለዳ እንጨት ያቃጥለበታል፤ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት በዚያ ላይ ይረበርባል፤ እንዲሁም የአንድነትን መሥዋዕት ስብ በዚያ ላይ ያቃጥላል።
“አሮንንና ልጆቹን እንዲህ ብለህ እዘዝ፦ የሚቃጠለው መሥዋዕት ሕግ ይህ ነው፤ የሚቃጠለው መሥዋዕት በመሠዊያው ላይ ባለው እንጨት ላይ ሌሊቱን ሁሉ እስኪጠባ ድረስ ይሆናል፤ የመሠዊያውም እሳት ዘወትር ይንደድበት።
እሳትም ከጌታ ዘንድ ወጣ፥ በመሠዊያውም ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ስቡንም በላ፤ ሕዝቡም ሁሉ አይተው እልል አሉ፥ በግምባራቸውም ተደፍተው ሰገዱ።