አቢሜሌክም አብርሃምን ጠርቶ አለው፦ “ይህ ያደረግህብን ምንድነው? ምንስ ክፉ ሠራሁብህ? በእኔና በመንግሥቴ ላይ ትልቅ ኃጢአት ያመጣህብን ምን ብንበድልህ ነው? ፈጽሞ የማይገባ ነገር በእኔ ፈጸምክብኝ።”
ዘሌዋውያን 4:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገር፦ ማናቸውም ሰው ባለማወቅ ጌታ አትሥሩ ካላቸው ትእዛዛት አንዱን ተላልፎ ኃጢአት ቢሠራ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ በላቸው፤ ‘ማንም ሰው ባለማወቅ ኀጢአት ቢሠራ፣ እግዚአብሔር አታድርጉ ብሎ ካዘዛቸውም አንዱን ተላልፎ ቢገኝ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ለእስራኤል ልጆች የምትነግራቸው ይህ ነው፦ ማንም ሰው ተሳስቶ ኃጢአት ቢሠራ ወይም ባለማወቅ ከእግዚአብሔር ትእዛዞች አንዱን ቢተላለፍ ከዚህ የሚከተለውን ሥርዓት ይጠብቅ፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ማናቸውም ሰው ሳያውቅ በእግዚአብሔር ፊት ኀጢአት ቢሠራ፥ እግዚአብሔርም፦ አትሥሩ ካላቸው ትእዛዛት አንዲቱን ቢተላለፍ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ማናቸውም ሰው ሳያውቅ ኃጢአት ቢሠራ፥ እግዚአብሔርም፦ አትሥሩ ካላቸው ትእዛዛት አንዲቱን ቢተላለፍ፥ |
አቢሜሌክም አብርሃምን ጠርቶ አለው፦ “ይህ ያደረግህብን ምንድነው? ምንስ ክፉ ሠራሁብህ? በእኔና በመንግሥቴ ላይ ትልቅ ኃጢአት ያመጣህብን ምን ብንበድልህ ነው? ፈጽሞ የማይገባ ነገር በእኔ ፈጸምክብኝ።”
በተንኰል ሳይሆን ድንገት ሳያስበው ባልንጀራውን ገድሎ ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዲቱ በመግባት ሕይወቱን ለማትረፍ ለሚሸሽ ሰው መመሪያው የሚከተለው ነው።
በሁለተኛይቱ ግን ሊቀ ካህናት ብቻውን በዓመት አንድ ጊዜ ይገባባታል፤ እርሱም ሰለ ራሱና ስለ ሕዝቡ ኃጢአት የሚያቀርበውን ደም ሳይዝ አይገባም፤
ነገር ግን ዮናታን አባቱ ሕዝቡን በመሐላ ማሰሩን አልሰማም ነበር። ስለዚህ በእጁ የያዘውን ዘንግ ጫፍ በማሩ ወለላ ውስጥ በማስገባት እጁን ወደ አፉ አደረገ፤ ዐይኑም በራ።