መክብብ 5:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 ብዙ ሕልም ባለበት፥ እንዲሁም ብዙ ቃል ባለበት፥ ብዙ ከንቱ ነገር አለ፥ አንተ ግን እግዚአብሔርን ፍራ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 አንደበትህ ወደ ኀጢአት እንዲመራህ አትፍቀድ፤ ለቤተ መቅደስ መልእክተኛም፣ “የተሳልሁት በስሕተት ነበር” አትበል። አምላክ በተናገርኸው ተቈጥቶ የእጅህን ሥራ ለምን ያጥፋ? Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 ወደ ኃጢአት እንዳይመራህ ለአንደበትህ ከገደብ ያለፈ ነጻነት አትስጠው፤ በዚህ ዐይነት “ይህን የተናገርኩት ሳላውቅ ነው” ብለህ በእግዚአብሔር አገልጋይ ፊት ይቅርታ ከመጠየቅ ትድናለህ፤ አለበለዚያ ግን የደከምክበትን ያጠፋ ዘንድ የእግዚአብሔርን ቊጣ በገዛ እጅህ እንደ መጋበዝ ይሆንብሃል። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 ለሥጋህ በደል አፍህን አትስጥ፥ በእግዚአብሔርም ፊት፥ “ባለማወቅ ነው” አትበል፤ እግዚአብሔር ስለ ቃልህ እንዳይቈጣ፥ የእጅህንም ሥራ እንዳያጠፋብህ፤ Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 ሥጋህን በኃጢአት እንዳያስተው ለአፍህ አርነት አትስጥ፥ በመልአክም ፊት፦ ስሕተት ነበረ አትበል፥ እግዚአብሔር በቃልህ ይቈጣ ዘንድ የእጅህንም ሥራ ያጠፋ ዘንድ ስለምን ትሻለህ? Ver Capítulo |