La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘሌዋውያን 23:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በዚህም ወር በዓሥራ አምስተኛው ቀን ለጌታ የቂጣ በዓል ነው፤ ሰባት ቀን እርሾ ያልነካው የቂጣ እንጀራ ትበላላችሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚያው ወር በዐሥራ ዐምስተኛው ቀን የእግዚአብሔር የቂጣ በዓል ይጀመራል፤ ለሰባት ቀንም ቂጣ ብሉ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዐሥራ አምስተኛው ቀን የቂጣ በዓል ይጀመራል፤ ከዚያን በኋላ እስከ ሰባት ቀን ድረስ እርሾ ያልነካው ቂጣ ትመገባላችሁ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በዚ​ህም ወር በዐ​ሥራ አም​ስ​ተ​ኛው ቀን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቂጣ በዓል ነው፤ ሰባት ቀን ቂጣ ብሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በዚህም ወር በአሥራ አምስተኛው ቀን ለእግዚአብሔር የቂጣ በዓል ነው፤ ሰባት ቀን ቂጣ እንጀራ ብሉ።

Ver Capítulo



ዘሌዋውያን 23:6
9 Referencias Cruzadas  

ይህም ቀን መታሰቢያ ይሁናችሁ፥ በዓል አድርጋችሁ ጠብቁት፥ ለጌታ በዓል ነው፤ ለትውልዳችሁ ለዘለዓለም ሥርዓት አድርጋችሁ ትጠብቁታላችሁ።


የቂጣውን በዓል ጠብቅ፤ በተመደበው በአቢብ ወር ሰባት ቀን ያልቦካ ቂጣ እንዳዘዝሁህ ትበላለህ፤ በዚህ ወር ከግብጽ ምድር ወጥታችኋልና፥ በፊቴም ባዶ እጃችሁን አትታዩ።


“የቂጣውን በዓል ጠብቀው፤ በአቢብ ወር ከግብጽ ወጥተሃልና በተወሰነው ጊዜ በአቢብ ወር እንዳዘዝሁህ ሰባት ቀን ቂጣ ብላ።


የቦካውን ቂጣ ከእርሱ ጋር አትብላ፥ ከግብጽ አገር በችኮላ ስለ ወጣህ ከግብጽ አገር የወጣህበትን ቀን በዕድሜህ ሁሉ ታስብ ዘንድ ይህን ቂጣ፥ እርሱም የመከራን እንጀራ፥ ሰባት ቀን ከእርሱ ጋር ብላ።


ስድስት ቀን ያልቦካ ቂጣ ብላ፤ በሰባተኛውም ቀን ለአምላክህ ለጌታ ጉባኤ ይሁን፤ በዚያ ቀን ሥራ አትሥራበት።