ዘሌዋውያን 23:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ለመወዝወዝ ቁርባን ነዶውን ካመጣችሁበት ቀን ከሰንበት በኋላ በማግስቱ ያሉትን ቀኖች ቁጠሩ። እነርሱም ሰባት ሙሉ ሳምንታት ይሁኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘የሚወዘወዘውን የነዶ መሥዋዕት ካቀረባችሁበት የሰንበት ማግስት አንሥታችሁ ሰባት ሙሉ ሳምንታት ቍጠሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ነዶአችሁን ለእግዚአብሔር በመወዝወዝ የሚቀርብ ልዩ መባ አድርጋችሁ ካመጣችሁበት ሰንበት ማግስት ጀምሮ ሰባት ሳምንት ቊጠሩ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ያቀረባችሁትን ነዶ ከምታመጡበት ቀን በኋላ ከሰንበት ማግስት ፍጹም ሰባት ሱባዔ ቍጠሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የወዘወዛችሁትን ነዶ ከምታመጡበት ቀን በኋላ ከሰንበት ማግስት ፍጹም ሰባት ጊዜ ሰባት ቀን ቍጠሩ፤ |
“ደግሞ በበኵራት ቀን ከሰባቱ ሱባዔ በዓላችሁ አዲሱን የእህል ቁርባን ለጌታ ባቀረባችሁ ጊዜ፥ የተቀደሰ ጉባኤ ይኑራችሁ፤ የጉልበት ሥራ ሁሉ አትሥሩበት።