La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘሌዋውያን 21:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የሚቀድስውም የአምላኩ የቅባዓት ዘይት በእርሱ ላይ ነውና ከመቅደስ አይውጣ፥ የአምላኩንም መቅደስ አያርክስ፤ እኔ ጌታ ነኝ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የተቀደሰበት የአምላኩ የቅብዐት ዘይት በላዩ ስለ ሆነ የአምላኩን መቅደስ ትቶ በመሄድ መቅደሱን አያርክስ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የእኔ የአምላኩ የክህነት ቅድስና በእርሱ ላይ ስላለ ከመቅደስ ወጥቶ የአምላኩን መቅደስ አያርክስ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የአ​ም​ላ​ኩም ቅባት ዘይት ቅዱ​ስ​ነት በላዩ ነውና ከመ​ቅ​ደስ አይ​ውጣ፤ የአ​ም​ላ​ኩ​ንም ቅዱስ ስም አያ​ር​ክስ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የአምላኩም ቅባት ዘይት ቅዱስነት በላዩ ነውና ከመቅደስ አይውጣ፥ የአምላኩንም መቅደስ አያርክስ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

Ver Capítulo



ዘሌዋውያን 21:12
9 Referencias Cruzadas  

ከንጹህ ወርቅ ቅጠል ሥራ፥ በእርሱም ላይ እንደ ማኅተም ቅርጽ ‘ለጌታ የተቀደሰ’ የሚል ቅረጽበት።


የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ ጌታ ቀብቶኛልና፥ ልባቸው የተሰበረውን እንድጠግን፥ ለተማረኩትም ነጻነትን፥ ለታሰሩትም መፈታትን እንዳውጅ ልኮኛል።


እንዲሁም የጌታ የቅባት ዘይት በላያችሁ ነውና እንዳትሞቱ ከመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አትውጡ።” እንደ ሙሴ ቃልም አደረጉ።


እርሱም ድንግል የሆነችውን ሴት ያግባ።


ሙሴም ከቅባቱ ዘይትና በመሠዊያው ላይ ካለው ከደሙ ወስዶ በአሮንና በልብሱ ላይ፥ በልጆቹና በልጆቹ ልብስ ላይ ረጨው፤አሮንንና ልብሱንም፥ ልጆቹንም፥ የልጆቹንም ልብስ ቀደሰ።


“ለጌታ ራሱን በለየበት ወራት ሁሉ ወደ ሬሳ አይቅረብ።


እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፤ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፤ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና፤