La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘሌዋውያን 21:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ለካህናቱ ለአሮን ልጆች እንዲህ ብለህ ለእነርሱ ተናገር፦ ማንም ሰው ከሕዝቡ መካከል ስለ ሞተው ራሱን አያርክስ፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ለካህናቱ ለአሮን ልጆች ንገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፤ ‘ማንኛውም ሰው ከዘመዶቹ መካከል ስለ ሞተው ሰው ራሱን አያርክስ፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ከሕዝቡ መካከል የሞተውን ሰው አስከሬን በመንካት ስለ ሞተ ሰው ማናቸውም ራሳቸውን እንዳያረክሱ የአሮን ተወላጆች ለሆኑ ካህናት ንገራቸው፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ሲል ተና​ገ​ረው፥ “ከወ​ገ​ና​ቸው በሞተ ሰው ራሳ​ቸ​ውን እን​ዳ​ያ​ረ​ክሱ ለካ​ህ​ናቱ ለአ​ሮን ልጆች ንገ​ራ​ቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔርም ሙሴን፦ ለካህናቱ ለአሮን ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው አለው፦ ማንም ሰው ከሕዝቡ ስለ ሞተው፥

Ver Capítulo



ዘሌዋውያን 21:1
12 Referencias Cruzadas  

እንዳይረክሱ ወደ ሞተ ሰው አይግቡ፤ ነገር ግን ለአባት ወይም ለእናት ወይም ለወንድ ልጅ ወይም ለሴት ልጅ ወይም ለወንድም ወይም ላላገባች እኅት ይርከሱ።


ካህናት ሆይ! ይህን ስሙ፤ የእስራኤል ቤት ሆይ! ልብ አድርጉ፤ የንጉሥ ቤት ሆይ! አድምጡ፤ በምጽጳ ላይ ወጥመድ፥ በታቦርም ላይ የተዘረጋ አሽክላ ሆናችኋልና ፍርድ በእናንተ ላይ ነው።


ስለ ሞተውም ብላችሁ ሥጋችሁን አትተልትሉ፥ ገላችሁንም ፈጽሞ አትንቀሱት፤ እኔ ጌታ ነኝ።


በድንም ወደ አለበት ስፍራ ሁሉ አይሂድ፥ ስለ አባቱም ወይም ስለ እናቱ አይርከስ።


“ካህናት ሆይ፥ አሁንም ይህ ትእዛዝ ለእናንተ ነው።


ቃል ኪዳኔ ከሌዊ ጋር ለማድረግ ይህን ትእዛዝ እንደ ላክሁላችሁ ታውቃላችሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።


“የሞተውን የማናቸውንም ሰው በድን የሚነካ ሰባት ቀን ርኩስ ይሆናል፤


“ሰው በድንኳን ውስጥ ቢሞት ሕጉ ይህ ነው፤ ወደ ድንኳኑ የሚገባ ሁሉ በድንኳኑም ውስጥ ያለው ሁሉ ሰባት ቀን ርኩስ ይሆናል።


በተንጣለለው ሜዳ በሰይፍ የተገደለውን ወይም የሞተውን በድን ወይም የሰውን ዐፅም ወይም መቃብር የሚነካ ማናቸውም ሰው ሰባት ቀን ርኩስ ይሆናል።


“የእስራኤል ልጆች የለምጽ ደዌ ያለበትን ሁሉ፥ ፈሳሽ ነገርም ያለበትን ሁሉ፥ ሬሳንም በመንካት የረከሰውን ሁሉ ከሰፈሩ እንዲያወጡ እዘዛቸው፤


“ለጌታ ራሱን በለየበት ወራት ሁሉ ወደ ሬሳ አይቅረብ።