ዘሌዋውያን 20:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ማናቸውም ሰው የአባቱን ልጅ ወይም የእናቱን ልጅ እኅቱን ቢያገባ፥ ኃፍረተ ሥጋዋንም ቢያይ፥ ኃፍረተ ሥጋውንም ብታይ፥ ይህ አሳፋሪ ነገር ነው፤ ከሕዝባቸውም ልጆች ፊት ተለይተው ይጥፉ፤ የእኅቱን ኃፍረተ ሥጋ ገልጦአልና በደሉን ይሸከማል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘አንድ ሰው የአባቱ ወይም የእናቱ ልጅ የሆነችውን እኅቱን አግብቶ ግብረ ሥጋ ቢፈጽም፣ አድራጎቱ አሳፋሪ ነው፤ በሕዝባቸው ፊት ከሕዝባቸው ተለይተው ይጥፉ። ሰውየው እኅቱን አዋርዷልና ይጠየቅበታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ሰው እኅቱን ወይም በአንድ በኩል ብቻ ከአባቱ ወይም ከእናቱ የተወለደችውን እኅቱን አግብቶ ፍትወታዊ ግንኙነት ቢያደርጉ ይህ አስነዋሪ ነገር በመሆኑ ከሕዝባቸው መካከል ተለይተው ይጥፉ፤ ከእኅቱ ጋር ፍትወታዊ ግንኙነት ስላደረገ ፍዳውን ይቀበላል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ማናቸውም ሰው የአባቱን ልጅ ወይም የእናቱን ልጅ እኅቱን ቢያገባ፥ ኀፍረተ ሥጋዋንም ቢያይ፥ እርስዋም ኀፍረተ ሥጋውን ብታይ፥ ይህ ጸያፍ ነገር ነው፤ በሕዝባቸውም ልጆች ፊት ይገደሉ፤ የእኅቱን ኀፍረተ ሥጋ ገልጦአልና ኀጢአቱን ይሸከማል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማናቸውም ሰው የአባቱን ልጅ ወይም የእናቱን ልጅ እኅቱን ቢያገባ፥ ኃፍረተ ሥጋዋንም ቢያይ፥ ኃፍረተ ሥጋውንም ብታይ፥ ይህ ጸያፍ ነገር ነው፤ በሕዝባቸውም ልጆች ፊት ይገደሉ፤ የእኅቱን ኃፍረተ ሥጋ ገልጦአልና ኃጢአቱን ይሸከማል። |
እርሷም እንዲህ አለችው፤ “አይሆንም፥ ወንድሜ፥ ተው አታስገድደኝ፤ እንዲህ ያለው ነገር በእስራኤል ተደርጎ አያውቅም፤ ይህን አስነዋሪ ድርጊት አትፈጽም።
ሰውም ከጎረቤቱ ሚስት ጋር ርኩሰትን አደረገ፥ ሌላውም የልጁን ሚስት በዝሙት አረከሰ፥ ሌላውም በአንቺ ውስጥ የአባቱን ልጅ፥ እኅቱን አዋረደ።
የእኅትህን ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ የአባትህ ልጅ ወይም የእናትህ ልጅ፥ በአገር ቤት ወይም በውጭ አገር የተወለደች ብትሆን፥ ኃፍረተ ሥጋዋን አትግለጥ።
አንዲት ሴት ወደ ማናቸውም እንስሳ ብትቀርብ፥ ከእርሱም ጋር ብትገናኝ፥ ሴቲቱንና እንስሳውን ግደል፤ ፈጽመው ይገደሉ፤ ደማቸው በራሳቸው ላይ ነው።