La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘሌዋውያን 2:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የምታቀርበውን የእህል ቁርባን ሁሉ በጨው ታጣፍጠዋለህ፤ የአምላክህንም የቃል ኪዳን ጨው ከእህል ቁርባንህ እንዳታጐድል፤ በቁርባንህ ሁሉ ላይ ጨው ታቀርባለህ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የምታቀርበውን የእህል ቍርባን ሁሉ በጨው ቀምመው፤ የአምላክህ የቃል ኪዳን ጨው ከእህል ቍርባንህ አይታጣ፤ በቍርባንህም ላይ ጨው ጨምርበት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ይህ የእህል ቊርባን ስለ ሆነ በእህል ቊርባንህ ሁሉ ላይ ጨው ጨምርበት፤ የአምላክህን የጨው ቃል ኪዳን አትተው፤ በቊርባኖች ሁሉ ጨው መግባት አለበት።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የም​ታ​ቀ​ር​ቡት ቍር​ባን ሁሉ በጨው ይጣ​ፈ​ጣል፤ የአ​ም​ላ​ክ​ህም ቃል ኪዳን ጨው ከቍ​ር​ባ​ንህ አይ​ጕ​ደል፤ በቍ​ር​ባ​ና​ችሁ ሁሉ ላይ ጨው ትጨ​ም​ራ​ላ​ችሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የምታቀርበውን የእህል ቍርባን ሁሉ በጨው ታጣፍጠዋለህ፤ የአምላክህንም ቃል ኪዳን ጨው ከእህል ቍርባንህ አታጐድልም፤ በቍርባንህ ሁሉ ላይ ጨው ታቀርባለህ።

Ver Capítulo



ዘሌዋውያን 2:13
8 Referencias Cruzadas  

የእስራኤል አምላክ ጌታ በእስራኤል ላይ መንግሥትን ለዳዊትና ለልጆቹ የጨው ቃል ኪዳን ለዘለዓለም እንደሰጠ በውኑ አታውቁምን?


እስከ መቶ መክሊት ብር፥ እስከ መቶ የቆሬስ መስፈሪያ ስንዴ፥ እስከ መቶ የባዶስ መስፈሪያ የወይን ጠጅ፥ እስከ መቶም የባዶስ መስፈሪያ ዘይት፥ ጨውም የሚፈልገውን ያህል ሳትጽፉ ስጡት።


ቀማሚ እንደሚቀምመው፥ በጨው የተቀመመ፥ ንጹሕና ቅዱስ አድርገህ ዕጣን አዘጋጅ።


በጌታ ፊት ታቀርባቸዋለህ፥ ካህናቱም በላያቸው ላይ ጨው ይነስንሱባቸው፥ ለጌታ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው ያቀርቡአቸዋል።


የእስራኤል ልጆች እንደ ስጦታ ከተቀደሰው ነገር ሁሉ አንሥተው ለጌታ ያቀረቡትን ለአንተ ከአንተም ጋር ለወንዶችና ለሴቶች ልጆችህ ድርሻ እንዲሆን ለዘለዓለም ሰጥቼሃለሁ፤ በጌታ ፊት ለአንተ ከአንተም ጋር ለዘርህ ለዘለዓለም የጨው ቃል ኪዳን ነው።”


እናንተ የምድሪቱ ጨው ናችሁ፤ ጨው ጣዕሙን ቢያጣ ግን በምን ይጣፍጣል? በሰው ለመረገጥ ወደ ውጭ ከመጣል በስተቀር ወደ ፊት ለምንም አይጠቅምም።


ለእያንዳንዱ እንዴት መልስ መስጠት እንደሚገባችሁ እንድታውቁ ንግግራችሁ ሁልጊዜ፥ በጨው እንደ ተቀመመ፥ በጸጋ ይሁን።