ደግሞም የተቀደሰ ኅብስት፥ ስስ ቂጣም ቢሆን፥ በምጣድም ቢጋገር፥ ቢለወስም፥ ለእህል ቁርባን በሆነው በመልካሙ ዱቄት በመስፈሪያና በመለክያ ሁሉ ያገልግሉ ነበር።
ዘሌዋውያን 19:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በፍርድ፥ በመለካትም፥ በመመዘንም፥ በመስፈርም አታታልሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘በመስፈሪያ ወይም በሚዛን አታጭበርብሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በርዝመት መለኪያ፥ በክብደት መለኪያና በመስፈሪያ አትበድሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በፍርድ፥ በመለካትም፥ በመመዘንም፥ በመስፈርም ዐመፃ አታድርጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በፍርድ፥ በመለካትም፥ በመመዘንም፥ በመስፈርም ዓመፃ አታድርጉ። |
ደግሞም የተቀደሰ ኅብስት፥ ስስ ቂጣም ቢሆን፥ በምጣድም ቢጋገር፥ ቢለወስም፥ ለእህል ቁርባን በሆነው በመልካሙ ዱቄት በመስፈሪያና በመለክያ ሁሉ ያገልግሉ ነበር።