ዘሌዋውያን 17:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም ከእስራኤል ልጆች በመካከላቸውም ከሚኖር እንግዳ ማናቸውም ሰው የሚበላ እንስሳ ወይም ወፍ አድኖ ቢይዝ፥ ደሙን ያፈስሳል በአፈርም ይሸፍነዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘እንዲበላ የተፈቀደውን ማንኛውንም እንስሳ ወይም ወፍ ዐድኖ የያዘ ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም በመካከላችሁ የሚኖር ማንኛውም መጻተኛ ደሙን ከውስጡ ያፍስስ፤ ዐፈርም ያልብሰው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ማናቸውም እስራኤላዊ ወይም በሕዝቡ መካከል የሚኖር መጻተኛ የሚበላ እንስሳ ወይም ወፍ አድኖ ቢይዝ ደሙን በመሬት ላይ አፍስሶ በዐፈር ይሸፍነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ከእስራኤልም ልጆች፥ ወይም በመካከላቸው ከሚኖሩ እንግዶች ማናቸውም ሰው የሚበላ እንስሳ ወይም ወፍ እያደነ ቢይዝ፥ ደሙን ያፈስሳል፤ በአፈርም ይከድነዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእስራኤልም ልጆች በመካከላቸውም ከሚኖሩ እንግዶች ማናቸውም ሰው የሚበላ እንስሳ ወይም ወፍ እያደነ ቢይዝ፥ ደሙን ያፈስሳል በአፈርም ይከድነዋል። |