La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘሌዋውያን 15:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ማንም ሰው ከእርሷ ጋር ተኝቶ የወር አበባዋ ቢነካው፥ እርሱ ሰባት ቀን ርኩስ ይሆናል፤ የሚተኛበትም መኝታ ሁሉ ርኩስ ይሆናል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ ‘አንድ ሰው ከርሷ ጋራ ቢተኛና የወር አበባዋ ቢነካው፣ እስከ ሰባት ቀን ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ እርሱ የሚተኛበት መኝታ ሁሉ ርኩስ ይሆናል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በወር አበባዋ ወቅት ከእርስዋ ጋር የሚተኛ ወንድ ቢኖር እርሱም እንደ እርስዋ የረከሰ ይሆናል፤ ስለዚህም እስከ ሰባት ቀን ድረስ ርኩስ ሆኖ ይቈያል፤ እርሱ የሚተኛበትም አልጋ ርኩስ ይሆናል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ማንም ከእ​ር​ስዋ ጋር ቢተኛ፥ ግዳ​ጅ​ዋም ቢነ​ካው፥ ሰባት ቀን ርኩስ ነው፤ የሚ​ተ​ኛ​በ​ትም መኝታ ሁሉ ርኩስ ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ማንም ከእርስዋ ጋር ቢተኛ መርገምዋ ቢነካው፥ ሰባት ቀን ርኩስ ነው፤ የሚተኛበትም መኝታ ሁሉ ርኩስ ነው።

Ver Capítulo



ዘሌዋውያን 15:24
9 Referencias Cruzadas  

በተራሮች ላይ ባይበላ፥ ዐይኖቹን ወደ እስራኤል ቤት ጣዖታት ባያነሣ፥ የባልንጀራውን ሚስት ባያረክስ፥ አደፍም ወዳለባት ሴት ባይቀርብ፥


በአንቺ ውስጥ የአባቶቻቸውን ዕራቁትነት ገለጡ፥ በአንቺም ውስጥ አደፍ ያለባትን አዋረዱ።


በመኝታም ወይም በማናቸውም ነገር ላይ ብትቀመጥ፥ እርሱ በሚነካው ጊዜ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።


እንዲሁም በወር አበባዋም ለታመመች፥ ፈሳሽም ነገር ላለባቸው ለወንድም ለሴትም፥ የረከሰችንም ሴት ለሚገናኝ ሰው ሕጉ ይህ ነው።


“እርሷም ርኩስ በሆነችበት የወር አበባዋ ጊዜያት ላይ ሳለች ኃፍረተ ሥጋዋን ለመግለጥ ወደ ሴት አትቅረብ።


ማናቸውም ሰው የወር አበባ ካለባት ሴት ጋር ቢተኛ ኃፍረተ ሥጋዋንም ቢገልጥ፥ ፈሳሽዋን ገልጦአልና፥ እርሷም የደምዋን ፈሳሽ ገልጣለችና ሁለቱ ከሕዝባቸው መካከል ተለይተው ይጥፉ።


ከማናቸውም ዓይነት ክፉ ነገር ራቁ።


ጋብቻ በሁሉ ዘንድ ክቡር፥ መኝታውም ንጹሕ ይሁን፤ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል።


ወዳጆች ሆይ! ባዕዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ ነፍስን ከሚዋጋ ሥጋዊ ምኞት ትርቁ ዘንድ እለምናችኋለሁ፤