Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘሌዋውያን 15:24 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 “ ‘አንድ ሰው ከርሷ ጋራ ቢተኛና የወር አበባዋ ቢነካው፣ እስከ ሰባት ቀን ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ እርሱ የሚተኛበት መኝታ ሁሉ ርኩስ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ማንም ሰው ከእርሷ ጋር ተኝቶ የወር አበባዋ ቢነካው፥ እርሱ ሰባት ቀን ርኩስ ይሆናል፤ የሚተኛበትም መኝታ ሁሉ ርኩስ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 በወር አበባዋ ወቅት ከእርስዋ ጋር የሚተኛ ወንድ ቢኖር እርሱም እንደ እርስዋ የረከሰ ይሆናል፤ ስለዚህም እስከ ሰባት ቀን ድረስ ርኩስ ሆኖ ይቈያል፤ እርሱ የሚተኛበትም አልጋ ርኩስ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ማንም ከእ​ር​ስዋ ጋር ቢተኛ፥ ግዳ​ጅ​ዋም ቢነ​ካው፥ ሰባት ቀን ርኩስ ነው፤ የሚ​ተ​ኛ​በ​ትም መኝታ ሁሉ ርኩስ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ማንም ከእርስዋ ጋር ቢተኛ መርገምዋ ቢነካው፥ ሰባት ቀን ርኩስ ነው፤ የሚተኛበትም መኝታ ሁሉ ርኩስ ነው።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 15:24
9 Referencias Cruzadas  

በኰረብታ ባሉ አብያተ ጣዖት የቀረበውን አይበላም፤ በእስራኤል ቤት ወዳሉት ጣዖታት አይመለከትም የባልንጀራውን ሚስት አያባልግም፤ ከሴት ጋራ በወር አበባዋ ጊዜ አይተኛም።


የአባታቸውን መኝታ የሚደፍሩ ሰዎች በውስጥሽ አሉ፤ በሥርዐቱ መሠረት ንጹሕ ባልሆኑበት በወር አበባቸው ጊዜ ሴቶችን በማስገደድ የሚደፍሩ በመካከልሽ ይገኛሉ።


መኝታዋን ወይም የተቀመጠችበትን ማንኛውንም ነገር የነካ ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።


በወር አበባ ላይ ያለችን ሴት፣ ፈሳሽ ነገር የሚወጣቸውን ወንድ ወይም ሴት፣ በሥርዐቱ መሠረት ርኩስ ከሆነች ሴት ጋራ የሚተኛውን ወንድ በሚመለከት ሕጉ ይኸው ነው።


“ ‘በወር አበባዋ ርኩሰት ጊዜ ግብረ ሥጋ ለመፈጸም ወደ ሴት አትቅረብ።


“ ‘ማንኛውም ሰው በወር አበባዋ ጊዜ ከሴት ጋራ ግብረ ሥጋ ቢፈጽም፣ የፈሳሿን ምንጭ ገልጧልና፣ እርሷም የፈሳሿን ምንጭ ገልጣለችና ሁለቱም ከሕዝባቸው መካከል ተለይተው ይጥፉ።


ከማንኛውም ዐይነት ክፉ ነገር ራቁ።


ጋብቻ በሁሉም ዘንድ ይከበር፤ መኝታውም ንጹሕ ይሁን፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር በአመንዝሮችና በሴሰኞች ሁሉ ላይ ይፈርዳል።


ወዳጆች ሆይ፤ በዚህ ዓለም እንግዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ መጠን፣ ነፍስን ከሚዋጋ ሥጋዊ ምኞት እንድትርቁ እለምናችኋለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios