La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘሌዋውያን 11:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከእነርሱም አንዱ በማናቸውም የሸክላ ዕቃ ውስጥ ቢወድቅ፥ በውስጡ ያለው ሁሉ ርኩስ ይሆናል፤ እናንተም ዕቃውን ትሰብሩታላችሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በድኑም በሸክላ ዕቃ ውስጥ ቢወድቅ፣ በውስጡ ያለ ነገር ሁሉ ርኩስ ስለሚሆን ዕቃውን ስበሩት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከነርሱ የአንዳቸው በድን በሸክላ ዕቃ ውስጥ ቢወድቅ፥ በዕቃው ውስጥ ያለው ነገር ሁሉ ስለሚረክስ፥ ሸክላውን ስበሩት።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከእ​ነ​ር​ሱም አን​ዳች በው​ስጡ የወ​ደ​ቀ​በ​ትን የሸ​ክ​ላ​ውን ዕቃ ሁሉ ስበ​ሩት፤ በው​ስ​ጡም ያለው ሁሉ ርኩስ ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከእነርሱም አንዳች በውስጡ የወደቀበትን የሸክላውን ዕቃ ሁሉ ስበሩት፥ በውስጡም ያለው ሁሉ ርኩስ ነው።

Ver Capítulo



ዘሌዋውያን 11:33
11 Referencias Cruzadas  

ሞዓብን ማንም እንደማይፈልገው ዕቃ ሰብሬዋለሁና በሞዓብ ሰገነት ሁሉ ላይ በአደባባዩም ላይ በሁሉም ቦታ ልቅሶ አለ፥ ይላል ጌታ።


እንዲህ ካለው ዕቃ ውኃ ፈስሶ የሚበላን ምግብ ሁሉ ከነካ ምግቡ ርኩስ ይሆናል፤ እንዲህም ካለው ዕቃ ሁሉ ማናቸውም የሚጠጣ መጠጥ በውስጡ ካለ እርሱ ርኩስ ይሆናል።


ከበድናቸውም የሚወድቅበት ነገር ሁሉ ርኩስ ይሆናል፤ እቶን ወይም ምድጃ ቢሆን ይሰበር፤ ርኩሶች ናቸው፤ በእናንተም ዘንድ ርኩሶች ይሆናሉ።


ልብሱን ያቃጥል፤ ድሩ ወይም ማጉ የበግ ጠጉር ወይም በፍታ ወይም ከተለፋው ቆዳ የሆነ ማናቸውም ደዌው ያለበት ነገር ላይ ቢሆን፥ እየሰፋ የሚሄድ የለምጽ ደዌ ነውና በእሳት ይቃጠል።


ቤቱንም፥ ድንጋዮቹንም፥ እንጨቱንም፥ የቤቱንም ምርጊት ሁሉ ያፈርሳል፤ እነርሱንም ከከተማው ውጭ ወደ ርኩስ ስፍራ ያወጣል።


ፈሳሽ ነገር ያለበት ሰው የሚነካውን የሸክላ ዕቃ ይሰብሩታል፤ የእንጨቱም ዕቃ ሁሉ በውኃ ይታጠባል።


ከዘይት ጋር በምጣድ ላይ ይዘጋጃል፤ ደኅና ተደርጎ ከተለወሰ በኋላ ታመጣዋለህ፤ ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን የተጋገረውን የእህል ቁርባን ቈራርሰህ ታቀርበዋለህ።


የሚቀቀልበትም ሸክላ ይሰበራል፤ ነገር ግን በናስ ዕቃ የተቀቀለ እንደሆነ ይፈገፈጋል፥ በውኃም ይለቀለቃል።


መክደኛው ያልታሰረ የተከፈተ ዕቃ ሁሉ ርኩስ ነው።


እርሱም ደግሞ ለራሱ ሁሉን ነገር በሥሩ ለማስገዛት በሚችልበት ኃይሉ ክቡር ሥጋውን እንዲመስል የተዋረደውን ሥጋችንን ይለውጣል።