ዘሌዋውያን 11:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን በውኆች ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ፥ በውኆች ውስጥም በሕይወት ከሚኖሩ ነፍሳት፥ በባሕሮችና በወንዞች ውስጥ ክንፍና ቅርፊት የሌላቸውን ሁሉ በእናንተ ዘንድ የተጸየፉ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን በባሕሮችና በወንዞች ውስጥ ከሚኖሩት ፍጥረታት ሁሉ፣ ከሚንፏቀቁት ወይም በውሃ ውስጥ ከሚኖሩት ሕይወት ካላቸው ሌሎች ፍጥረታት መካከል ክንፍና ቅርፊት የሌላቸው በእናንተ ዘንድ አስጸያፊዎች ይሁኑ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን በውሃ ውስጥ የሚገኘው ክንፍና ቅርፊት የሌለው ፍጥረት ሁሉ መበላት የለበትም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በውኆች ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ፥ በውኆች ውስጥ የሕይወት ነፍስ ከአላቸው ሁሉ፥ በባሕሮችና በወንዞች ውስጥ ክንፍና ቅርፊት የሌላቸው ሁሉ በእናንተ ዘንድ የተጸየፉ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውኆች ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ፥ በውኆች ውስጥ የሕይወት ነፍስ ካላቸው ሁሉ፥ በባሕሮችና በወንዞች ውስጥ ክንፍና ቅርፊት የሌላቸው ሁሉ በእናንተ ዘንድ የተጸየፉ ናቸው። |
“በውኃ ውስጥ ከሚኖሩት ሁሉ እነዚህን ትበላላችሁ፤ በውኆች በባሕሮችም በወንዞችም ውስጥ ከሚኖሩት ሁሉ ክንፍና ቅርፊት ያላቸውን ትበላላችሁ።
በሦስተኛው ቀን ከአንድነቱ መሥዋዕት ከቶ ሥጋ ቢበላ፥ አይሠምርለትም ላቀረበው ሰው የተጠላ ይሆንበታል እንጂ ቁርባን ሆኖ አይቈጠርለትም፤ ሰውም ከእርሱ ቢበላ ኃጢአቱን ይሸከማል።
ነገር ግን የሚፈሩ፥ የማያምኑ፥ የሚረክሱ፥ ነፍሰ የሚያጠፉ፥ የሚሴሰኑ፥ አስማትን የሚያደርጉ፥ ጣዖትንም የሚያመልኩና የሚዋሹ ሁሉ ዕጣ ክፍላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ውስጥ ነው፤ ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።”