Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 11:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ነገር ግን በባሕሮችና በወንዞች ውስጥ ከሚኖሩት ፍጥረታት ሁሉ፣ ከሚንፏቀቁት ወይም በውሃ ውስጥ ከሚኖሩት ሕይወት ካላቸው ሌሎች ፍጥረታት መካከል ክንፍና ቅርፊት የሌላቸው በእናንተ ዘንድ አስጸያፊዎች ይሁኑ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ነገር ግን በውኆች ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ፥ በውኆች ውስጥም በሕይወት ከሚኖሩ ነፍሳት፥ በባሕሮችና በወንዞች ውስጥ ክንፍና ቅርፊት የሌላቸውን ሁሉ በእናንተ ዘንድ የተጸየፉ ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ነገር ግን በውሃ ውስጥ የሚገኘው ክንፍና ቅርፊት የሌለው ፍጥረት ሁሉ መበላት የለበትም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 በው​ኆች ውስጥ ከሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀሱ፥ በው​ኆች ውስጥ የሕ​ይ​ወት ነፍስ ከአ​ላ​ቸው ሁሉ፥ በባ​ሕ​ሮ​ችና በወ​ን​ዞች ውስጥ ክን​ፍና ቅር​ፊት የሌ​ላ​ቸው ሁሉ በእ​ና​ንተ ዘንድ የተ​ጸ​የፉ ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 በውኆች ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ፥ በውኆች ውስጥ የሕይወት ነፍስ ካላቸው ሁሉ፥ በባሕሮችና በወንዞች ውስጥ ክንፍና ቅርፊት የሌላቸው ሁሉ በእናንተ ዘንድ የተጸየፉ ናቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 11:10
10 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር፣ “ውሆች ሕይወት ባላቸው በሕያዋን ፍጥረታት ይሞሉ፤ ወፎች ከምድር በላይ በሰማይ ጠፈር ይብረሩ” አለ።


ከጠቢብ ጋራ የሚሄድ ጠቢብ ይሆናል፤ የሞኝ ባልንጀራ ግን ጕዳት ያገኘዋል።


ጻድቃን አታላዮችን ይጸየፋሉ፤ ክፉዎችም ቅኖችን ይጠላሉ።


በእናንተ ዘንድ አስጸያፊ ስለ ሆኑ ሥጋቸውን አትብሉ፤ በድናቸውንም ትጸየፋላችሁ፤


“ ‘በባሕሮችና በወንዞች ውሃ ውስጥ ከሚኖሩት ፍጥረታት ክንፍና ቅርፊት ያላቸውን መብላት ትችላላችሁ፤


ማንኛውም የኅብረት መሥዋዕት ሥጋ በሦስተኛው ቀን ከተበላ ተቀባይነት የለውም፤ ርኩስ በመሆኑ ላቀረበው ሰው ዋጋ አይኖረውም፤ ከዚያም የበላ ሰው የበደል ዕዳ ይሆንበታል።


ክንፍና ቅርፊት የሌለውን ግን አትብሉ፤ ለእናንተ ርኩስ ነው።


ማንኛውንም ርኩስ ነገር አትብላ።


ነገር ግን ፈሪዎች፣ የማያምኑ፣ ርኩሶች፣ ነፍሰ ገዳዮች፣ አመንዝሮች፣ አስማተኞች፣ ጣዖት አምላኪዎች፣ ውሸተኞች ሁሉ ዕጣ ፈንታቸው በዲንና በእሳት ባሕር ውስጥ መጣል ይሆናል። ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos