ሰቈቃወ 5:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለግብጻውያንና ለአሦራውያን እንጀራ እንጠግብ ዘንድ እጅ ሰጠን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንጀራ እንጠግብ ዘንድ፣ ለአሦርና ለግብጽ እጃችንን ሰጠን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቂ ምግብ ለማግኘት ለግብጽና ለአሦር እጃችንን ሰጠን፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ግብፃውያንና አሦራውያን፥ እንጀራን ያጠግቡን ዘንድ እጃቸውን ሰጡን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለግብጻውያንና ለአሦራውያን እንጀራ እንጠግብ ዘንድ እጅ ሰጠን። |
ኢዩ ተነሥቶ እንደገና ጉዞ ቀጠለ፤ በመንገድ ሳለም የሬካብን ልጅ ኢዮናዳብን አገኘ፤ ኢዩም ሰላምታ ከሰጠው በኋላ “እኔና አንተ በሐሳብ አንድ ነን፤ ታዲያ ከእኔ ጋር ትተባበራለህን?” ሲል ጠየቀው። ኢዮናዳብም “አዎ እተባበርሃለሁ” ሲል መለሰ። ኢዩም “እንግዲያውስ ጨብጠኝ” ሲል መለሰለት፤ እጅ ለእጅ ተያይዘው ኢዩ ደግፎት በሠረገላው ላይ አስቀመጠውና፥
አሁንስ የሺሖርን ውኃ ለመጠጣት ወደ ግብጽ በመሄድሽ የምታገኚው ምን ነገር አለ? የኤፍራጥስንም ውኃ ለመጠጣት ወደ አሦር በመሄድሽ የምታገኚው ምን ነገር አለ?
የጌታ በቀል ነውና በዙሪያዋ ሆናችሁ በእርሷ ላይ ጩኹ፤ እጅዋን ሰጠች፤ ግንቦችዋ ወደቁ ቅጥሮችዋም ፈረሱ፤ እርሷን ተበቀሉ እንደ ሠራችውም ሥሩባት።
ኤፍሬምም ደዌውን፥ ይሁዳም ቁስሉን ባየ ጊዜ ኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ፥ ወደ ታላቁም ንጉሥ መልእክተኛን ላከ፤ እርሱ ግን ሊፈውሳችሁ፥ ከቁስላችሁም ሊያድናችሁ አልቻለም።