ሰቈቃወ 3:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብርሃን ወደሌለበት ወደ ጨለማ መርቶ ወሰደኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከፊቱ አስወጣኝ፤ በብርሃን ሳይሆን በጨለማ እንድሄድ አደረገኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምንም ብርሃን ወደሌለበት ጨለማ መርቶ ወሰደኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብርሃን ወደሌለበት ወደ ጨለማ መርቶ ወሰደኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብርሃን ወደ ሌለበት ወደ ጨለማ መርቶ ወሰደኝ። |
ስለዚህ ፍርድ ከእኛ ዘንድ ርቆአል፥ ጽድቅም አላገኘንም፤ ብርሃንን በተስፋ እንጠባበቅ ነበር፥ እነሆም፥ ጨለማ ሆነ፤ ጸዳልን በተስፋ እንጠባበቅ ነበር፥ ነገር ግን በጨለማ ሄድን።
ሳትጨልም እግራችሁም በጨለሙት ተራሮች ላይ ሳትሰናከል፥ በተስፋ የምትጠባበቁትን ብርሃን ለሞት ጥላና ለድቅድቅ ጨልማ ሳይለውጠው፥ ለአምላካችሁ ለጌታ ክብርን ስጡ።
አሌፍ። ጌታ በቁጣው የጽዮንን ሴት ልጅ እንደምን አደመናት! የእስራኤልን ውበት ከሰማይ ወደ ምድር ጣለ፥ በቁጣውም ቀን የእግሩን መረገጫ አላሰበም።
በእኩለ ቀን ዕውር በዳበሳ እንደሚሄደው ትሄዳለህ። የምታደርገው ሁሉ አይሳካልህም። ዘወትር ትጨቆናለህ፤ ያለማቋረጥም ትመዘበራለህም፤ የሚታደግህ አይኖርም።
የገዛ ነውራቸውን አረፋ የሚደፍቁ እየባሰ የሚሄድ የባሕር ማዕበል ናቸው፤ ድቅድቅ ጨለማ ለዘለዓለም የተዘጋጀላቸው የሚንከራተቱ ከዋክብት ናቸው።
የመጀመሪያ ቦታቸውን ያልጠበቁትን ነገር ግን መኖሪያቸውን የተዉትን መላእክት በዘለዓለም እስራት እስከ ታላቁ ቀን ፍርድ ድረስ ከጨለማ በታች ጠብቆአቸዋል።