መጽሐፈ ዮዲት 11:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምድር ሁሉ ንጉሥ፥ ሕያው ፍጥረትን ሁሉ እንድታቀና በላከህ ናቡከደነፆርና በኃይሉ እምላለሁ፤ በአንተ በኩል ሰዎች ብቻ የሚገዙለት አይደሉም፤ ነገር ግን የዱር አራዊትና ከብቶች፥ በሰማይ የሚበሩ ወፎችም በኃይልህ ከናቡከደነፆርና ከቤቱ በታች ይገዙለታል እንጂ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምድር ሁሉ ንጉሥ ናቡከደነፆር በሕይወት ይኑር! ፍጥረቱን ሁሉ ታቀና ዘንድ አንተን የላከ ኀይሉ ይኑር። በምድረ በዳ የሚኖሩ አውሬዎችና እንስሳ፥ በሰማይ የሚበሩ ወፎችም በኀይልህ ከናቡከደነፆርና ከቤቱ በታች ይኖራሉ እንጂ በዘመንህ ሰዎች ብቻ የሚገዙለት አይደለም። |