መሳፍንት 9:46 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሴኬም ግምብ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ይህን እንደ ሰሙ፤ በኤልበሪት ቤተ መቅደስ ወዳለው ምሽግ ውስጥ ገቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሴኬም ግንብ ውስጥ የሚኖሩ ገዦች ይህን እንደ ሰሙ፤ በኤልበሪት ቤተ መቅደስ ወዳለው ምሽግ ውስጥ ገቡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሴኬም ግንብ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ይህን በሰሙ ጊዜ ባዓልበሪት በሚመለክበት ቤት በሚገኘው ምሽግ ውስጥ ገቡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሰቂማም ግንብ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ሁሉ ይህን በሰሙ ጊዜ ወደ በዓል ቤት ወደ ምሽጉ ውስጥ ገቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሴኬምም ግንብ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ሁሉ ይህን በሰሙ ጊዜ ወደ ኤልብሪት ቤት ወደ ምሽጉ ውስጥ ገቡ። |
በአምላኩም በናሳራክ ቤት ሲሰግድ ልጆቹ አድራሜሌክና ሳራሳር በሰይፍ ገደሉት፤ ወደ አራራትም አገር ኰበለሉ። ልጁም አስራዶን በእርሱ ፈንታ ነገሠ።