መሳፍንት 7:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌዴዎንም በኤፍሬም ኰረብታማ አገር ለሚኖሩት ሁሉ፥ “በምድያማውያን ላይ ውረዱ፤ እስከ ቤትባራ ድረስ ያለውንም የዮርዳኖስ ወንዝ ቀድማችሁ ያዙ” አላቸው። ስለዚህ የኤፍሬም ሰዎች ሁሉ ተጠርተው ወጡ፤ እስከ ቤትባራ ድረስ ያለውንም የዮርዳኖስን ወንዝ ያዙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌዴዎንም መልእክተኞቹን ልኮ፣ በኤፍሬም ኰረብታማ አገር ለሚኖሩት ሁሉ፣ “በምድያማውያን ላይ ውረዱ፤ እስከ ቤትባራ ድረስ ያለውንም የዮርዳኖስ ወንዝ ቀድማችሁ ያዙ” አላቸው። ስለዚህ የኤፍሬም ሰዎች ሁሉ ተጠርተው ወጡ፤ እስከ ቤትባራ ድረስ ያለውንም የዮርዳኖስን ወንዝ ያዙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌዴዎንም በኮረብታማው በኤፍሬም አገር ወዳሉት ሁሉ መልእክተኞች ልኮ “ወርዳችሁ በምድያማውያን ላይ ዝመቱ፤ ምድያማውያን ተሻግረው እንዳያመልጡ የዮርዳኖስን ወንዝና ወደ እርሱ የሚገቡትንም መጋቢ ወንዞች እስከ ቤትባራ ድረስ በር በሩን ዘግታችሁ በተጠናከረ ሁኔታ ጠብቁ” አላቸው። ስለዚህ የኤፍሬም ሰዎች በአንድነት ተጠራርተው የዮርዳኖስን ወንዝና ወደዚያ የሚገቡትን መጋቢ ወንዞች እስከ ቤተባራ ድረስ ዘግተው ያዙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌዴዎንም፥ “ምድያማውያንን ለመግጠም ውረዱ፥ እስከ ቤትባራም ድረስ ያለውን ውኃ፥ ዮርዳኖስንም፥ ያዙባቸው” ብሎ መልእክተኞችን በኤፍሬም ወዳለው ተራራማ ሀገር ሁሉ ላከ። የኤፍሬምም ሰዎች ሁሉ ተሰብስበው እስከ ቤትባራ ድረስ ውኃውን፥ ዮርዳኖስንም ቀድመው ያዙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌዴዎንም፦ ምድያምን ለመገናኘት ውረዱ፥ እስከ ቤትባራም ድረስ ያለውን ውኃ፥ ዮርዳኖስን፥ ያዙባቸው ብሎ መልክተኞችን በኤፍሬም ወዳለው ተራራማ አገር ሁሉ ሰደደ። የኤፍሬም ሰዎችም ሁሉ ተሰብስበው እስከ ቤትባራ ድረስ ውኃውን፥ ዮርዳኖስን፥ ያዙ። |
ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ ብቻ ኑሩ፤ በዚህም መጥቼ ባያችሁ ወይም ብርቅ፥ በአንድ ልብ ስለ ወንጌል እምነት አብራችሁ መጋደላችሁንና በአንድ መንፈስ ጸንታችሁ መቆማችሁን እሰማለሁ።
ገለዓዳውያን ወደ ኤፍሬም የሚያሻግሩትን የዮርዳኖስን መሻገሪያዎች ያዙ፤ ታድያ አምልጦ የሚሸሽ አንድ ኤፍሬማዊ ለመሻገር በሚጠይቃቸው ጊዜ፥ የገለዓድ ሰዎች “አንተ ኤፍሬማዊ ነህ?” ብለው ይጠይቁታል፤ ያም ሰው፥ “አይደለሁም” ብሎ ከመለሰላቸው፥
እግዚአብሔር የምድያማውያንን መሪዎች ሔሬብንና ዜብን በእጃችሁ አሳልፎ ሰጣችሁ፤ታዲያ እናንተ ከፈጸማችሁት ጋር የሚወዳደር ምን ማድረግ እችል ነበር?” ይህን ሲሰሙ ቊጣቸው በረደ።