መሳፍንት 12:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 ገለዓዳውያን ወደ ኤፍሬም የሚያሻግሩትን የዮርዳኖስን መሻገሪያዎች ያዙ፤ ታድያ አምልጦ የሚሸሽ አንድ ኤፍሬማዊ ለመሻገር በሚጠይቃቸው ጊዜ፥ የገለዓድ ሰዎች “አንተ ኤፍሬማዊ ነህ?” ብለው ይጠይቁታል፤ ያም ሰው፥ “አይደለሁም” ብሎ ከመለሰላቸው፥ Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 ገለዓዳውያን ወደ ኤፍሬም የሚያሻግሩትን የዮርዳኖስን መልካዎች ያዙ። ታዲያ አምልጦ የሚሸሽ አንድ ኤፍሬማዊ ለመሻገር በሚጠይቃቸው ጊዜ፣ የገለዓድ ሰዎች “አንተ ኤፍሬማዊ ነህ?” ብለው ይጠይቁታል፤ ያም ሰው፣ “አይደለሁም” ብሎ ከመለሰላቸው፣ Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 የኤፍሬም ሰዎች እንዳያመልጡ ለማድረግ ገለዓዳውያን የዮርዳኖስን መሻገሪያ ቦታዎች ሁሉ ዘግተው ያዙ፤ ለማምለጥ የሚሞክር ማንኛውም የኤፍሬም ሰው ለመሻገር ፈቃድ ቢጠይቅ ገለዓዳውያን “አንተ የኤፍሬም ሰው ነህን?” ብለው ይጠይቁት ነበር፤ “አይደለሁም!” ካለ፥ Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 የገለዓድ ሰዎችም ኤፍሬም በሚያልፍበት በዮርዳኖስ ማዶ ደረሱባቸው። ከዚህ በኋላ ከኤፍሬም ያመለጡት እንሻገር ባሉ ጊዜ የገለዓድ ሰዎች፥ “በውኑ እናንተ ከኤፍሬም ወገን ናችሁን?” ቢሉአቸው “አይደለንም” አሉ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 ገለዓዳውያንም ኤፍሬም የሚያልፍበትን የዮርዳኖስን መሻገርያ ያዙባቸው፥ የሸሸም የኤፍሬም ሰው፦ ልለፍ ባለ ጊዜ፥ የገለዓድ ሰዎች፦ አንተ ኤፍሬማዊ ነህን? አሉት፥ እርሱም፦ አይደለሁም ቢል፥ Ver Capítulo |