Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 7:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 እንዲሁም ሔሬብና ዜብ የተባሉትን ሁለቱን የምድያም መሪዎች ያዙ። ሔሬብን በሔሬብ ዐለት አጠገብ፥ ዜብን ደግሞ በዜብ የወይን መጭመቂያ ላይ ገደሏቸው፤ ምድያማውያንንም አሳደዱ፤ የሔሬብንና የዜብን ራስ ቈርጠው ጌዴዎን ወዳለበት ወደ ዮርዳኖስ ይዘው መጡ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 እንዲሁም ሔሬብና ዜብ የተባሉትን ሁለቱን የምድያም መሪዎች ያዙ። ሔሬብን በሔሬብ ዐለት አጠገብ፣ ዜብን ደግሞ በዜብ የወይን መጭመቂያ ላይ ገደሏቸው፤ ምድያማውያንንም አሳደዱ፤ የሔሬብንና የዜብን ራስ ቈርጠው ጌዴዎን ወዳለበት ወደ ዮርዳኖስ ይዘው መጡ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ዖሬብና ዘኤብ የተባሉ ሁለት የምድያማውያን መሪዎችንም ማረኩ፤ ዖሬብን “የዖሬብ አለት” ተብሎ ወደሚጠራው ስፍራ፥ ዘኤብንም “የዘኤብ የወይን መጭመቂያ” ተብሎ በሚጠራው ቦታ ገደሉአቸው፤ ከዚህም በኋላ የቀሩትን ምድያማውያን ማሳደድ ቀጠሉ፤ የዖሬብንና የዘኤብንም ራሶች ቈርጠው ወደ ጌዴዎን አመጡለት፤ በዚያን ጊዜ ጌዴዎን ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ በኩል ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 የም​ድ​ያ​ምን ሁለ​ቱን አለ​ቆች ሔሬ​ብ​ንና ዜብን ያዙ፤ ሔሬ​ብ​ንም በሱ​ር​ኤ​ራብ ገደ​ሉት፥ ዜብ​ንም በኢ​ያ​ፌቅ ገደ​ሉት፤ የም​ድ​ያ​ም​ንም ሰዎች አሳ​ደዱ፤ የሔ​ሬ​ብ​ንና የዜ​ብ​ንም ራስ ይዘው ወደ ዮር​ዳ​ኖስ ማዶ ወደ ጌዴ​ዎን አመጡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 የምድያምን ሁለቱን መኳንንት ሔሬብንና ዜብን ያዙ፥ ሔሬብንም በሔሬብ ዓለት አጠገብ ገደሉት፥ ዜብንም በዜብ መጥመቂያ ላይ ገደሉት፥ ምድያምንም አሳደዱ፥ የሔሬብንና የዜብንም ራስ ይዘው ወደ ዮርዳኖስ ማዶ ወደ ጌዴዎን መጡ።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 7:25
7 Referencias Cruzadas  

እንደ ምድያምና እንደ ሲሣራ፥ በቂሶንም ወንዝ እንደ ኢያቢስ አድርግባቸው።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድያምን በሔሬብ ዐለት አካባቢ እንደ መታ፤ በጅራፍ ይገርፋቸዋል፤ በግብጽ እንዳደረገውም ሁሉ፤ በትሩን በውሆች ላይ ያነሣል።


የጦረኞች ጫማ ሁሉ፤ በደም የተለወሰ ልብስም ሁሉ፤ ለእሳት ይዳረጋል፤ ይማገዳልም።


የኢትዮጵያ ድንኳኖች በጭንቀት ላይ ሆነው አየሁ፥ የሚድያን ምድር መጋረጃዎች ተንቀጠቀጡ።


በእርሱም ላይ እስከ ዛሬ ድረስ ያለ ታላቅ የድንጋይ ክምር ከመሩ፤ ጌታም ከጽኑ ቁጣው ተመለሰ። ስለዚህም የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ የአኮር ሸለቆ ተብሎ ተጠራ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos