ውኃ እጠጣ ዘንድ እንስራሽን አዘንብዪ የምላት እርሷም አንተ ጠጣ፥ ግመሎችህን ደግሞ አጠጣለሁ የምትለኝ ቆንጆ፥ እርሷ ለባርያህ ለይስሐቅ ያዘጋጀሃት ትሁን፥ በዚህም ለጌታዬ ምሕረትን እንዳደረግህ አውቃለሁ።”
መሳፍንት 7:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚሉትንም አድምጥ፤ ከዚያ በኋላ በሰፈሩ ላይ አደጋ ለመጣል ድፍረት ታገኛለህ፤” ስለዚህም ጌዴዎን አገልጋዩን ፉራን አስከትሎ እስከ ሰፈሩ ዳርቻ ወረደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚሉትንም ስማ፤ ከዚያ በኋላ በሰፈሩ ላይ አደጋ ለመጣል ድፍረት ታገኛለህ።” ስለዚህም ጌዴዎን አገልጋዩን ፉራን አስከትሎ እስከ ሰፈሩ ዳርቻ ወረደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም የሚሉትን ትሰማለህ፤ ከዚያም በኋላ በእነርሱ ላይ አደጋ ለመጣል ድፍረት ታገኛለህ፤”። ስለዚህ ጌዴዎንና አገልጋዩ ፑራ ወደ ጠላት ሰፈር ዳርቻ ወረዱ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚናገሩትንም አድምጣቸው፤ ከዚያም በኋላ እጆችህ ይበረታሉ፤ ወደ ሰፈርም ትወርዳለህ” አለው። እርሱም ከሎሌው ፋራን ጋር ከሰፈሩ በአንድ ወገን የአምሳ አለቃ ጦር ወደ ሰፈረበት ወረደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚናገሩትንም ትሰማለህ፥ ከዚያም በኋላ ወደ ሰፈሩ ትወርድ ዘንድ እጅህ ትበረታለች አለው። እርሱና ሎሌው ፉራ በሰፈሩ ዳርቻ ወደ ነበሩት ሰልፈኞች ወረዱ። |
ውኃ እጠጣ ዘንድ እንስራሽን አዘንብዪ የምላት እርሷም አንተ ጠጣ፥ ግመሎችህን ደግሞ አጠጣለሁ የምትለኝ ቆንጆ፥ እርሷ ለባርያህ ለይስሐቅ ያዘጋጀሃት ትሁን፥ በዚህም ለጌታዬ ምሕረትን እንዳደረግህ አውቃለሁ።”
ጌታ ደስ አሰኝቶአቸዋልና፥ የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ቤትም ለመሥራት እጃቸውን እንዲያጸኑ የአሦርን ንጉሥ ልብ ወደ እነርሱ መልሶአልና የቂጣውን በዓል ሰባት ቀን በደስታ አከበሩ።
ነገር ግን እግዚአብሔር ሕዝቡን ዞረው በኤርትራ ባሕር ባለችው ምድረ በዳ መንገድ መራቸው። የእስራኤልም ልጆች ከግብጽ ምድር ለጦርነት ተሰልፈው ወጡ።
የፍልስጥኤም ጦር ሰፈር ሰዎችም፥ “ኑ ወደ እኛ ውጡ፤ የምናሳያችሁ ነገር ይኖራል” ሲሉ በዮናታንና በጋሻ ጃግሬው ላይ ጮኹባቸው። ስለዚህ ዮናታን ጋሻ ጃግሬውን፥ “ተከትለኸኝ ውጣ፤ ጌታ በእስራኤላውያን እጅ አሳልፎ ሰጥቷቸዋልና” አለው።
ዳዊትም ሒታዊውን አቢሜሌክንና የጸሩያን ልጅ የኢዮአብን ወንድም አቢሳን፥ “ወደ ሳኦል ሰፈር አብሮኝ የሚወርድ ማነው?” ሲል ጠየቃቸው። አቢሳም፥ “እኔ አብሬህ እወርዳለሁ” አለ።